የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

የጤና ባለሙያዎች የማበረታቻ አበል መመሪያ እንዲተገበር ወሰነ

ኢዛ (ዓርብ ግንቦት ፲፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. May 22, 2020)፦ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ኢኮኖሚው ላይ የሚያሳደረውን ተጽእኖ ለመቋቋም፣ የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት ያስፈልጋሉ የተባሉ ወጪዎችን ለመሸፈን የ2012 በጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት አዋጅን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አጸደቀ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤቱ ዛሬ ዓርብ ግንቦት 14 ቀን ባካሔደው 83ኛ ስብሰባው የ2012 ተጨማሪ በጀትን አዋጅ ከማጽደቅ ጎን ለጎን የመካከለኛ ዘመን ተብሎ የተጠቅሰውና ከ2013 - 2017 በጀት ዓመት የማክሮ ኢኮኖሚና ፊዚካል ማዕቀፍ ላይም ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል።

በዛሬው የሚኒስትሮች ምክር ቤት 83ኛ መደበኛ ስብሰባ በአጠቃላይ ሰባት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ያስተላለፈ ሲሆን፤ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ የጤና ባለሙያዎች የማበረታቻ አበል ክፍያ የሚያገኙበት መመሪያም ጸድቋል።

የዛሬው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ያሳለፈባቸው ጉዳዮች ውስጥ ቀሪዎቹ የሚከተሉት ናቸው። የጂኦተርማል ሀብት ልማት አዋጅን ለማሻሻል የቀረብው ረቂቅ አዋጅ አንዱ ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ ለሕዝብ ጥቅም መሬት ሲለቀቅ ስለሚከፈል ካሣ እና የልማት ተነሺዎችን መልሶ ስለማቋቋም በወጣው የሚኒስትሮች ደንብ ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማካተት በነጋሪት ጋዜጣ ትቶ እንዲወጣና በሥራ ላይ እንዲውል መወሰኑ ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!