Mr. Melaku Alebel, Minister of Ministry of Trade and Industry

አቶ መላኩ አለበል (የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር)

ከ2,100 በላይ ነጋዴዎች ጉዳያቸው በሕግ የተያዘ ነው

ኢዛ (ረቡዕ ግንቦት ፳፮ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 3, 2020)፦ የዋጋ ጭማሪ በማድረጋቸውና በገበያ ውስጥ እጥረት እንዲፈጠር ሠርተዋል የተባሉ ከ64 ሺህ 900 (64,900) በላይ የሚኾኑ ሕገወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ ገለጹ።

ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እንደገለጹት፤ ወቅታዊውን የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት አድርገው በግብይት ውስጥ እጥረት እንዲፈጠርና ዋጋ ጭማሪ አድርገዋል የተባሉት እነዚህ ሕገወጥ ነጋዴዎች ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተገኙ ናቸው።

በመላ አገሪቱ በተሰበሰበው መረጃ መሠረት እርምጃ ከተወሰደባቸው እነዚህ ነጋዴዎች ውስጥ፤ ኾን ብለው ገበያው እንዳይረጋጋና እጥረት ለመፍጠር ሲሠሩ የነበሩ፣ የሸማቾች ሕብረት ሥራ ማኅበራትን የሚመሩ ግለሰቦችም ይገኙባቸዋል ተብሏል።

በተለይ መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ ዋጋ በመጨመር የተሳተፉ ከ2,100 በላይ ነጋዴዎች ጉዳያቸው በሕግ የተያዘ ነው። 460 ደግሞ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል ተብሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ