ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ፖርላማ ይቀርባሉ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
ስብሰባው የሚካሔደው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ነው
ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 8, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተገኝተው፤ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ሰኔ 1 ቀን 2012 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ አምስተኛውን ልዩ ስብሰባውን የሚያካሒድ ሲሆን፤ ዋና ጉዳዩም የምክር ቤቱ አባላት በሚቀርብ ጥያቄ መሠረት ምላሽና ማብራሪያ የሚሰጡበት ይሆናል። (ኢዛ)



