Total coronavirus cases in Ethiopia, June 20, 2020

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የሁኔታ መግለጫ (ቅዳሜ ሰኔ 13 ቀን 2012 ዓ.ም.፤ በጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ)

በአንድ ቀን 399 ሰዎች ቫይረሱ ተገኘባቸው

ኢዛ (ቅዳሜ ሰኔ ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 20, 2020)፦ በአስጊ ሁኔታ እየሰፋ የመጣው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ በየዕለቱ በቫይረሱ የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመሔድ፤ በአንድ ቀን ብቻ 399 ሰዎች መገኘታቸውን የሚያመለክት ሪፖርት ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 13 ቀን ይፋ ኾኗል።

በኢትዮጵያ ቫይረሱ መከሰቱ ከተገለጸበት ሦስት ወር ወዲህ ከፍተኛ ተጠቂዎች የተገኙበት ኾኑ የተመዘገበበት ቀን ኾኗል።

ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበበት ቀን ከመኾኑም በላይ የቫይረሱ ሥርጭት እየጨመረ መኾኑን የሚያመለክተው 399 ተጠቂዎች የተገኙት 4,848 ሰዎች ተመርምረው መኾኑ ነው። ባለፉት ሦስት ወሮች ከዚህም በላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተመርማሪዎች በነበሩበት የ24 ሰዓት ሪፖርት ወቅት የተጠቂዎቹ ቁጥር ከዚህ ያነሰ እንደነበር ይታወሳል።

በዛሬው የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት አዲስ 399 ተጠቂዎች መገኘታቸው፤ በአገሪቱ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 4,469 አድርሶታል።

በአንጻሩ ግን ዛሬም 95 ያገገሙ ሰዎች በመገኘታቸው፤ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች 1,122 ሊደርስ ችሏል። በዛሬው ሪፖርት ሞት ያልተመዘገበ በመኾኑ፤ የሟቾች ቁጥር 72 ላይ ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ