Jawar Mohammed

አቶ ጃዋር መሐመድ

በዕለቱ ይሰማሉ የተባሉ ምስክሮች ቃል ሳይሰማ ቀርቷል፤ ፍርድ ቤቱም በመጥሪያ እስኪጠሩ ማረሚያ ቤት ይቆዩ ብሏል

ኢዛ (ሰኞ ነኀሴ ፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 10, 2020)፦ ዛሬ ነኀሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም. በቀጠሮ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ጃዋር በዓቃቤ ሕግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ማሰማት በጀመረበት ወቅት፤ እነአቶ ጃዋር ዳኛው ከመዝገባቸው ይነሳላቸው ዘንድ አቤቱታ በማቅረባቸው ምስክሮች ሳይሰማ ቀረ።

በእነአቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ዛሬ የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ማሰማት በጀመረበት ወቅት እነአቶ ጃዋር ዳኛው ከመዝገባችን ይነሳልን በማለት ባቀረቡት አቤቱታ ምክንያት ፍርድ ቤቱ አቤቱታውን በመመልከት ትእዛዝ ሰጥቷል።

ይኽም በአቤቱታው መሠረት ተመልክቶ ዳኛው መዝገቡ እንዲመረመርና በመዝገቡ ላይ ትእዛዝ እስኪሰጥበት ድረስ እነአቶ ጃዋር በማረሚያ ቤት እንዲቆዩና መጥሪያ ሲደርሳቸው እንዲመጡ ትእዛዝ በመስጠት መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ብሏል።

እነአቶ ጃዋር ዳኛው ገለልተኛ ላይኾን ይችላል በሚል ያቀረቡት አቤቱታ በሰባት ገጽ የተደገፈ እንደነበር ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ