የ1954ቱ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት እንዲሻሻል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወሰነ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
በሌሎች ጉዳዮችም ውሳኔ አሳልፏል
ኢዛ (ቅዳሜ መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 26, 2020)፦ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሔደው 90ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ የ1954ቱን የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓት እና የማስረጃ ረቂቅ አዋጅ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ውሳኔ አሳለፈ።
ምክር ቤቱ በ90ኛው መደበኛ ስብሰባው ውሳኔ ያሳለፈበት ተመሳሳይ ጉዳይ፤ የግልግል ዳኝነትን እና የእርቅ አሠራር ረቂቅ አዋጅ ነው።
የአክሪዲቴሽን አገልግሎት ክፍያ ረቂቅ ደንብ እንዲተገበር ውሳኔ ላይ ስለመድረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር የተያያዙ ሌሎች ጉዳዮች ላይም በመወያየት ከውሳኔ ላይ ደርሷል። ምክር ቤቱ በዛሬው ስብሰባው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በተመለከተ ይፋ ያደረገው መረጃ የሚከተለው ነው። (ኢዛ)





