Presidant Isaias Afwerki and PM Dr. Abiy Ahmed

ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂና ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ቡና ሲለቅሙ

በኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት ላይ ይመክራሉ ተብሏል

ኢዛ (ሰኞ ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. October 12, 2020)፦ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በሦስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን፤ አቀባበል የተደረገላቸው በጅማ ከተማ ነው።

የአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂን የሦስት ቀናት ጉብኝት አስመልክቶ በተሰራጨው መረጃ፤ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ስላለው ግንኙነትና በምሥራቅ አፍሪካ አገራት መካከል ስለሚኖረው ትስስር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ይመክራሉ ተብሏል።

ፕሬዝዳንቱ በጅማ አባ ጅፋር አየር ማረፊያ ሲደርሱ በቦታው የተቀበሉዋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅማ ጎማ ወረዳ ውስጥ የሚገኘውንና የተዳቀለ የቡና ዝርያ በኩታ ገጠም እርሻ የሚመረትበትን ስፍራ ለፕሬዝዳንቱ አስጎብኝተዋቸዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ