Ethiopia Zare (ሰኞ ጥቅምት ፫-3 ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 13, 2008)፦ ትናንት እሁድ ጥቅምት 2 ቀን 2001 ዓ.ም. ማምሻውን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በውጭ ሀገር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የመገናኛ ብዙኀን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ። ፓርቲውን በመወከል የተገኙት ሊቀመንበሯ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሣ ናቸው።

 

ጋዜጣዊ መግለጫው የተካሄደው በቴሌኮንፈረንስ ሲሆን፣ አንድ ሰዓት ከአርባ ስድስት ደቂቃዎች አካባቢ ፈጅቷል። ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሣ አንድነት ፓርቲ ያለበትንና ባለፉት ሦስት ወራት ሲሠራቸው የነበሩትን አንዳንድ ጉዳዮች ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኀን ከተገኙ ጋዜጠኞችና ተወካዮች የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

 

ይህንኑ ጋዜጣዊ መግለጫ በድምፅ ለማድመጥ ይቻልዎ ዘንድ ከዚህ በታች አቅርበነዋል። የማጫወቻ ቁልፉን በመጫን ያድምጡ!

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ