Dr. Mulu Nega

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ - ዶ/ር ሙሉ ነጋ

በጊዜያዊ አስተዳደሩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ይካተታሉ

ኢዛ (ዓርብ ኅዳር ፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. November 13, 2020)፦ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኾነው እንዲያገለግሉ ዶ/ር ሙሉ ነጋ መሰየማቸው ተገለጸ። ሹመቱን የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ናቸው።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት በትግራይ ብሔራዊ ክልል የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ማጽደቅን ተከትሎ የተወሰደ እርምጃ ነው።

የዋና ሥራ አስፈጻሚው ኃላፊነትን በተመለከተ እንደተገለጸው፤ ዋና ሥራ አስፈጻሚው የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል ኾነው የክልሉን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት የሚመሩ ኃላፊዎችን በመመልመል ይሾማሉ።

እነዚህ ኃላፊዎች በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመመልመል የሚሾሙ መኾኑንም መረጃው ያመለክታል።

ዶ/ር ሙሉ የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ በመኾን ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ