የአንድነት የግጥም ምሽት በፖሊስ ለአንድ ሰዓት ታገደ
Ethiopia Zare (ኀሙስ ጥቅምት ፮ ቀን ፳፻፩-2001 ዓ.ም. October 16, 2008)፦ ዛሬ ማምሻውን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ አዘጋጅቶት የነበረው የግጥም ምሽት ”ፈቃድ የላችሁም” በሚል በፖሊስ ታግዶ የነበረ ሲሆን፣ በዚሁ ምክንያት ከታቀደበት ሰዓት ለአንድ ሰዓት ያህል ዘግይቶ ተጀምሯል። ተሳታፊዎችን ፖሊስ አግዷቸው በነበረበት ወቅት
አዲስ አበባ ውስጥ በተለምዶ ላንቻ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው አጎና ሲኒማ አንድነት ፓርቲ ”ሀገር ማለት” በሚል ርዕስ ያዘጋጀው የሥነ ጽሑፍ ምሽት ላይ በርካታ ተሳታፊዎች ተገኝተው እንደነበርና ፖሊስ ለአንድ ሰዓት ያህል በፈቃድ ሰበብ አግዶት የነበረ ቢሆንም በስተመጨረሻ ግን ጉዳዩ እልባት ማግኘቱን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።
በዚሁ የግጥም ምሽት ላይ ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ፣ ፕ/ር መስፍንና በርካታ ወጣቶች ግጥሞቻቸውን በንባብ አሰምተዋል።