Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 9 ቀን 2001 ዓ.ም. October 19, 2008)፦ የኢትዮጵያን ሚሌኒየምን ለማክበር በከፍተኛ ባለሥልጣናት ስብስብ የተቋቋመው ብሔራዊ ሚሌኒየም ም/ቤት፣ ትናንት ቅዳሜ ጥቅምት 8 ቀን 2001 ዓ.ም. ያለፈውን የሥራ ውጤቱን ገምግሞ በይፋ ተዘግቷል። በዚሁ በሼራተን ሆቴል በተካሄደው ሥነሥርዓት ላይ የጽ/ቤቱ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሥዩም በረደድ ጽ/ቤቱ ካቀዳቸው 16 ፕሮጀክቶች ግማሹ ያለመሳካታቸውን በሪፖርታቸው ገልፀዋል።

 

የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ብሔራዊ ምክር ቤት፣ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 117/97 መሠረት በአዋጅ ነበር የተቋቋመው። ይኼ ምክር ቤት ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆኖ፤ ፕሬዚዳንቱ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የግብርናና የገጠር ልማት ሚኒስትር አቶ አዲሱ ለገሰ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን እንዲሁም የክልል ፕሬዚዳንቶቹን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት የካቲት 29 ቀን 1999 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል ሲሰበሰቡ ከሀገሪቱ መሪዎች ታላቅ ነገር ተጠብቆ ነበር።

 

የበዓል አከባበር ምክር ቤቱ፣ በዋና ዳይሬክተሩ ለሚመራው የጽ/ቤት ሠራተኞች ታህሣሥ 4 ቀን 1999 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ላይ የተቋቋመበትን የሁለት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድና የድርጊት መርኀ ግብር አቅርቦ ካፀደቀ በኋላ በማርሽ ባንድ አጅቦ፣ ዓርማውን ሲያስመርቅ የነበረው የሒልተን ሆቴል ሽር ጉድ ለብሔራዊ ምክር ቤቱ ቀጣይ የሥራ አፈፃፀም ግርማ ሞገስ ሰጥቶት ነበር።

 

የሚሌኒየሙ በዓል አከባበር የተሳካ ነበር ወይ? በሚል ምክር ቤቱ የተቋቋመበትን ዓላማና የሥራ ውጤት በተመለከተ፣ የተለያዩ ሰዎችን በማነጋገር ውስጥ የሚታተመው እንቢልታ ጋዜጣ ”የተሳካ ሚሌኔየም?” በሚል ርዕስ በመስከረም 23 ቀን 2001 ዓ.ም. ዕትሙ ሰፋ ያለ ዘገባ አቅርቦ ነበር። (ሙሉ ዘገባውን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ