ለምርጫ 2013 ወደ ቅስቀሳ የገቡና እየገቡ ያሉ ፓርቲዎች

ለምርጫ 2013 ወደ ቅስቀሳ የገቡና እየገቡ ያሉ ፓርቲዎች

ፓርቲዎች ወደ ምርጫ ቅስቀሳ እየገቡ ነው

ኢዛ (ቅዳሜ የካቲት ፲፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 20, 2021)፦ በቀጣይ አገራዊ ምርጫ የምርጫ ማኒፌስቶዋቸውን በማስተዋወቅ ብልጽግናና ኢዜማ ቀዳሚ ኾነዋል። ሌሎች ፓርቲዎችም ወደ ቅስቀሳ እየገቡ ነው።

በሳምንቱ አጋማሽ ላይ ብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ማኒፌስቶውን የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለትም ኢዜማ የምርጫ ማኒፌስቶውን ይፋ ያደርጋል።

በቀጣዩ ምርጫ ዝግጅቶች ዙሪያ ከሌሎች ፓርቲዎች በተለየ ብልጽግናና ኢዜማ ምርጫው ላይ አተኩረው እየሠሩ ስለመኾኑ እያደረጉዋቸው ያሉት እንቅስቃሴዎች እያሳዩ ነው።

ሁለቱ ፓርቲዎች በመላ አገሪቱ በምርጫው ተፎካካሪ ለመኾን እየሠሩ መገኘታቸው በቀጣዩ ምርጫ ዋነኛ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ኾነው እንደሚቀርቡ እያሳዩ ነው።

የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ በዚህ ሳምንት መጀመር እንደሚችል ከተገለጸ በኋላ፤ ይፋዊ ቅስቀሳ ከጀመሩት ከብልጽግናና ኢዜማ ሌላ አብን እና ባልደራስ በነገው ዕለት ቅስቀሳ እንደሚጀምሩ ታውቋል።

ምርጫን በተመለተ ከሰሞኑ እንደተሰማው ኦነግ በዚህ ምርጫ መሳተፍ አለመሳተፉን ያልለየ ሲሆን፤ በአመራሮቹ ደረጃ የተፈጠረው መከፋፈል የምርጫ ዝግጅት እያደረገ ያለመኾኑን አመላክቷል።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ አቶ ቀጄላ መርዳሳ እንዳስታወቁትም፤ እስካሁን እጩ ለማዘጋጀት ያለመቻሉን ሲሆን፣ ለምርጫው ዝግጁ ለማድረግ ያላስቻላቸው ደግሞ የተከፋፈለው የፓርቲው አመራር ማካሔድ የሚገባው ጠቅላላ ጉባዔ ማድረግ ባለመቻሉ ነው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ