የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ውጭ ስብሰባው ተካሔደ

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፲፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. February 22, 2021)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በአገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ የካቢኔ ስብሰባቸውን በኮይሻ እያካሔዱ ነው።

ምንጮች እንደገለጹት ካቢኔያቸውን ይዘው በደቡብ ክልል በኮይሻ ከተማ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባቸው ዋነኛ አጀንዳ የግማሽ ዓመት ብሔራዊ የሥራ ክንውን ምዘና ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ይህንንም የምክር ቤቱን ስብሰባ በመምራት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዛሬው የካቢኔ ስብሰባ አስመልክተው በማኅበራዊ ገጻቸው ላይ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የስደስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሔደ መኾኑን ገልጸው፤ “በየስድስት ወሩ የምናካሒደውን እያንዳንዱን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የሥራ ክንውን ግምገማ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት ጋር በመኾን ጀምረናል” ብለዋል።

በጸደቀው ዓመታዊ ዕቅድ መሠረት ቀጣይነት ያለውን ምዘና መከወናችን፣ የተስተዋሉ ክፍተቶችን በመሙላት እና አስፈጻሚ አካላት ተጠያቂ እንዲኾኑ በማድረግ ለዜጎች ተገቢው አገልግሎት መቅረቡን ለማረጋገጥ ያስችላል ሲሉም ገልጸዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀውም የስብሰባ ቦታውን ባይጠቅስም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአዲስ አበባ ውጭ እየመሩ ላሉት ስብሰባ ላይ በጸደቀው ዓመታዊ ዕቅድ መሠረት ቀጣይነት ያለውን ምዘና መካሔዱ ክፍተቶችን በሙላት እና አስፈጻሚ አካላት ተጠያቂ ያደርጋል ማለታቸውን ጠቅሷል። እንዲሁም ለዜጐች ተገቢውን አገልግሎት መቅረቡን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል።

ሁሉም የካቢኔ አባላት የተካፈሉበት በዚህ ስብሰባ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶቹ በግማሽ ዓመቱ ያሳኳቸውን ተግባራት እና ያጋጠሙዋቸውን ችግሮች በዝርዝራ አቅርበዋል ተብሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ