የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ሜቴክ (አሁን ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ)፣ ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን፣ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የስኳር ኮርፖሬሽን

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ሜቴክ (አሁን ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ)፣ ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን፣ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የስኳር ኮርፖሬሽን

የአብዛኛውን ብድር የወሰዱት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው

ኢዛ (ዓርብ መጋቢት ፲፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 26, 2021)፦ ከፍተኛ የአገር ውስጥ ብድር ካለባቸው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውስጥ ሰባቱ ብቻ ከ780 ቢሊዮን ብር በላይ (ከ19 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ) እዳ እንዳለባቸው ተገለጸ።

የገንዘብ ሚኒስቴር ዛሬ ዓርብ መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ማምሻውን ይፋ አደረገው በተባለው መረጃ፤ በብድር የተዘፈቁት ሰባቱ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ ሜቴክ (አሁን ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ)፣ ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን፣ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የስኳር ኮርፖሬሽን ናቸው።

እነዚህ ድርጅቶች በአብዛኛውን ብድር የወሰዱት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለው አጠቃላይ ሀብት (አሴት) አንድ ትሪልዮን ብር ነው። እነዚህ ሰባት የመንግሥት ድርጅቶች ብቻ ያለባቸው እዳ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካለው አጠቃልይ አሴት ውስጥ 78 በመቶውን ያኽላል።

መንግሥት ባደገው ግምገማ እነዚህ ድርጅቶች ከ780 ቢሊዮን ብር በላይ፣ በአሜሪካ ከ19 ቢሊዮን ዶላር በላይ እዳ እንዳለባቸው ማረጋገጥ የቻለ ሲሆን፤ ባለፉት 10 ዓመታት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ብድር በ21 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የዛሬው መረጃ ያሳያል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ