PM Abiy Ahmed while visiting Homicho Ammunition Engineering

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ “ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ” በጎበኙበት ወቅት

የጎበኙት በአሁን አጠራሩ “ሆሚቾ” የተሰኘውንና በደርግ ዘመን የተመሠረተውን “ታጠቅ ኢንጂነሪንግ ፋብሪካ”ን ነው

ኢዛ (እሁድ መጋቢት ፲፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 28, 2021)፦ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን በማምረት የሚጠቀሰውን “ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ” ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ተገብኝቷል።

የዛሬውን ጉብኝታቸውን አስመልክቶ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት፤ መከላከያ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ ምርቶችን በማምረት በዚህም የራሱን ቁመና አጠናክሮ ወትሮ ዝግጅቱን በማሳደግ በምርምር የሚልቅበትን መሠረታዊ ሪፎርም መጀመሩን አይቻለሁ ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ “ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ” በጎበኙበት ወቅት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ “ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ” በጎበኙበት ወቅት

አያይዘውም ይህን አጠንክረን በመቀጠል መከላከያችን ሁለንተናዊ የተቋም ቁመና እንዲኖረው ቀጣይ ሥራዎች እንደሚሠሩም አመልክተዋል።

የአገር መከላከያ ሠራዊት የማምረት አቅሙን አጠናክሮ በዘላቂነት የአገር ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲገኝ ሪፎርም መጀመሩን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዛሬ የጎበኙት ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ሪፎርሙ ትልቅ መሠረት የጣል መኾኑን የሚያሳይ እንደኾነም ጠቅሰዋል።

ሆሚቾ ቀደም ብሎ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ (ሜቴክ) ሥር ካሉ ተቋማት መካከል አንዱ ሲሆን፤ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎችን የሚያመርት ኢንዱስትሪ ነው። በሪፎርሙ መሠረት እንደአዲስ ተደራጅቶ እንዲሠራ የተደረገ መኾኑንም ለማወቅ ተችሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ “ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ” በጎበኙበት ወቅት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ “ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ” በጎበኙበት ወቅት

ይህ ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ የተገነባው በደርግ ዘመን በ1979 ዓ.ም. ላይ “ታጠቅ ኢንጂነሪንግ ፋብሪካ” ተብሎ ሲሆን፤ በወቅቱ በተለይም የቀላልና የባድ መሣሪዎች ጥይቶችን ለማምረት እንደነበር ይታወሳል። ከጅምሩ የሞርታር ጥይቶችን ይሠራ የነበር ሲሆን፤ በኋላም የረዥም ርቀት ተወንጫፊ ጥይቶችን ማምረት ችሏል።

ሕወሓት/ኢሕአዴግ አገሪቷን ከተቆጣጠር በኋላ ሜቴክን በማቋቁም፤ በደርግ ዘመን እና በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን የተቋቋሙትን ከመከላከያ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች በሙሉ በሥሩ የጠቀለላቸው ሲሆን፤ ታጠቅ ኢንጂነሪንግንም በ1996 ዓ.ም. ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ብሎ ስሙን መቀየሩ ይታወቃል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ