Mekele

መቀሌ

ከምሽቱ አንድ ሰዓት የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ ወደ ሁለት ሰዓት ተራዘመ

ኢዛ (ረቡዕ መጋቢት ፳፪ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. March 31, 2021)፦ ላለፉት አራት ወራት በትግራይ ክልል ተፈጻሚ እየኾነ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተደነገገው የሰዓት እላፊ ገደብ ማሻሻያ እንደተደረገበት ተገለጸ።

ለዚሁ ማስፈጸሚያ የሚኾን መመሪያ ወጥቶ እየተተገበረ መኾኑን የሚገልጸው መረጃ፤ በዚህም መሠረት ከምሽቱ አንድ ሰዓት የነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ ወደ ሁለት ሰዓት እንዲራዘም ተደርጓል።

በክልሉ ያለው ሰላም እየተሻሻለ በመምጣቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ይበልጥ እንዲነቃቃ ለማስቻል የተወሰደ እርምጃ ነው ተብሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ