Ambassador Tibor Nagy

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

እንደገና ምርጫውን ለመታዘብ ፍላጎት አለኝ አለ

ኢዛ (ቅዳሜ ሚያዝያ ፴ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 8, 2021)፦ በኢትዮጵያ የሚካሔደውን ስድስተኛውን አገር አቀፍ ምርጫ 2013 ታዛቢዎቼን አልክም ብሎ አሳውቆ የነበረው የአውሮፓ ሕብረት፤ አሁን ደግሞ ምርጫውን የሚታዘቡ ኤክስፐርቶች እልካለሁ ማለቱ ተሰማ።

ዛሬ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ፤ ታዛቢዎችን የመላኬን እቅድ ሰርዣለሁ ብሎ አሳውቆ የነበረ ቢኾንም፤ አሁን ግን ምርጫውን የሚታዘቡ ኤክስፐርቶች የመላክ ፍላጎት እንዳለው ማሳወቁን ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ምርጫውን ለመታዘብ ጥያቄ ያቀረቡ የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ምርጫውን ለመታዘብ ዝግጅታቸውን ገልጸው የመታዘብ ሒደቱም ኢትዮጵያ ቀደም ሲል የተቀመጡትን ቅድም ሁኔታዎች ባደረገ ሁኔታ የሚፈጸም እንደሚኾንም መጥቀሳቸው ተነግሯል።

የአውሮፓ ሕብረት የቀደመውን ሐሳቡን ለውጦ ምርጫውን የሚታዘቡ ኤክስፐርቶችን ለመላክ ፍላጎቱን ማሳየቱን እንጂ፤ ዝርዝር ማብራሪያ ያልተሰጠበት ቢኾንም፤ በደፈናው ታዛቢዎቹ ቀደም ብሎ ኢትዮጵያ ያስቀመጠችውን ቅድመ መስፈርት መሠረት ባደረገ መልኩ የሚፈጸም እንደሚኾን ከዛሬው የቃል አቀባዩ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ