አማኑኤል ወንድሙ

ወጣት አማኑኤል ወንድሙ፣ በታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል በድምቢ ዶሎ፣ ቄለም ወለጋ ዞን ማክሰኞ ግንቦት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. የተገደለ

ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀቡም ጠይቋል

ኢዛ (ረቡዕ ግንቦት ፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 12, 2021)፦ በኦሮሚያ ክልል በድምቢ ዶሎ፣ ቄለም ወለጋ ዞን ትናንት ግንቦት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አንድ በወንጀል ተጠርጣሪን በአደባባይ መግደላቸውን በመጥቀስ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ግድያውን ኮንኗል።

ኮሚሽኑ አስደንጋጭ ያለውን ይህንን ድርጊት፤ ወጣቱ ከሕግ አግባብ ውጭ የተገደለ መኾኑን ገልጾ፤ ግድያው ሕዝብ እያየ መኾኑን ጭምር ጠቅሷል።

በጸጥታ ኃይሎች የተገደለው ወጣት አማኑኤል ወንድሙ፤ ከመገደሉ በፊት ድብደባ የተፈጸመበትና እንዲሁም ወደኋላ ታስሮ እንደነበር ተንቀሳቃሽ የቪዲዮ ምስሎች ጭምር ታይተው ነበር።

ከሕግ ውጭ ማንኛውም ዐይነት ግድያዎችን በብርቱ የሚያወግዘው ኮሚሽኑ፤ የጸጥታ ኃይሉ የሕግ ማስከበር ሥራዎችን በሕግ አግባብ መፈጸም እንዳለበትም በዚሁ መግለጫው ላይ አመልክቷል። ድርጊቱ የሕግ የበላይነትን የሚጻረር ስለመኾንም ኮሚሽኑ ሳይጠቅስ አላለፈም።

አሁንም በወጣት አማኑኤል ወንድሙ ግድያ ላይ አስቸኳይ ምርመራ ተደርጎ አጥፊዎች አስፈላጊው ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድም ኮሚሽኑ ጠይቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ