PM Abiy Ahmed

ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ትውልድ ቀያቸው የምረጡኝ ቅስቀሳ ለማድረግ ጅማ ከተማ ሲገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምርጫ ቅስቀሳ ወደ ትውልድ መንደራቸው ሔዱ

ኢዛ (ረቡዕ ሰኔ ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 16, 2021)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ትውልድ ቀያቸው የምረጡኝ ቅስቀሳ ለማድረግ ጅማ ከተማ ገብተዋል።

በፓርቲዎች የመጨረሻ ቅስቀሳ ማጠቃለያ ቀን ወደ ጅማ ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ወደ ተወለዱበት በሻሻ በመሔድ ብልጽግና ይመረጥ ዘንድ የምርጫ 2013 ቅስቀሳቸውን ያከናውናሉ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጅማ መጓዝን ተከትሎ ጅማ እና አካባቢዋ እንኳን ደኅና መጡ በሚሉ መፈክሮች እና የድጋፍ ማስታወቂያዎችና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶዎች ተሸፍነዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምርጫ ቅስቀሳ ባሻገር በጀማ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የሚመርቁ ሲሆን፤ ለከተማዋ ነዋሪዎችም ንግግር አድርገዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ