PM Abiy Ahmed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ

እናመሰግናችኋለን ብለዋቸዋል

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፳፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 28, 2021)፦ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ 2013 በተደረገ በአንደኛ ሳምንቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በምርጫው ከተወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ጋር መምከራቸውና ምስጋና ማቅረባቸው ተገለጸ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ እንዳመለከቱት “ኢትዮጵያ አሸናፊ ኾና የወጣችበት ሰላማዊ ምርጫ እንዲሳካ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ብለዋል።

ገና በጅምር ያለው ዴሞክራሲያችንን ለማጠናከር በምርጫ ሒደቱ ውስጥ የታዩ ተግዳሮቶች እና ክፍተቶችን በመገምገም ምን እንደተማርንባቸው ተወያይተንበታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የውይይቱን ይዘት ዝርዝር ጉዳይ ግን እስካሁን አልተገለጸም። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ