Ethiopia Zare (ቅዳሜ ጥር 24 ቀን 2000 ዓ.ም. February, 2,2008)፦በአቶ አየለ ጫሚሶ የሚመራውና በምርጫ ቦርድ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲን ሕጋዊ ሠርተፊኬት የተሰጠው ፓርቲ ከሌሎች ሁለት ፓርቲዎች ጋር በጥምረት ለምርጫ ለመዘጋጀትና ብሎም ለመዋሃድ ንግግር ጀምረዋል።

ከትናንት በስቲያ ዓርብ ዕለት ከሰዓት በኋላ ላይ ብርሃን ለአንድነትና ለዴሞክራሲ (ብአዴ) እና የመላው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ንቅናቄ (መኢብን) አመራሮች ከአቶ አየለ ጫሚሶ ቅንጅት ጋር ለመወያየት ቀጠሮ ተይዞላቸው ነበር። እነኝህን ፓርቲዎች ያገናኙዋቸው የቅንጅት አባል የነበሩት አቶ ማንአለኝ ፈረደ እንደሆኑ ምንጮቻችን ገልጠዋል።

በተያዘው የቀጠሮ ሰዓት የብርሃን ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲው ሊቀመንበር ሙላቱ ጣሠው መገኘት ያልቻሉ ሲሆን፣ የመኢብን (የመላው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ንቅናቄን) ወክለው አቶ መስፍን ሽፈራው እንዲሁም ቅንጅቱን ወክለው አቶ አየለ ጫሚሶ እና አቶ ሳሳሁልህ ከበደ ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በምርጫ 97ቱ አራቱ ፓርቲዎች ተጣምረው "ቅንጅት"ን ፈጥረው ውጤት እንዳመጡት ሁሉ በመጪው ምርጫ ለየብቻቸው ሆነው እርስ በእርሳቸው ከመወዳደር ይልቅ ጥምረት ፈጥረው በምርጫው ለመሳተፍ ተስማምተዋል። ቀጣይ ቀጠሮ የቆረጡ ሲሆን፣ በሚቀጥለው ቀጠሮ ሁሉም ተገኝተው በሠፊው ለመወያየት ተስማምተዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ