የማነ ገብረመስቀል

የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል

በጄኔቭ የኤርትራ ኤምባሲ በጉዳዮ ላይ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር እየተነጋገረበት ነው

ኢዛ (ሰኞ ሐምሌ ፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 12, 2021)፦ በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሕወሓት ቡድን በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የበቀል እርምጃ እየወሰደ መኾኑን ኤርትራ ገለጸች።

የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል እንዳስታወቁት፤ የሕወሓት ቡድን በስደተኛ ጣቢያ ውስጥ ባሉ ንጹኀን ኤርትራውያን ላይ በበቀል ተነሳስቶ ጭፍጨፋ እየፈጸመ መኾኑን አስታውቀዋል።

ቡድኑን በዚህን ያህል ደረጃ እየፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ በግልጽ እየታወቀ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የመገናኛ ብዙኀን ጉዳዩን ችላ ማለታቸውንም ሚኒስትሩ በዛሬው (ሰኞ ሐምሌ 5 ቀን 2013 ዓ.ም.) መረጃቸው አስታውቀዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በጄኔቭ የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ጉዳዩን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ጋር የተነጋገረበት ሲሆን፣ በሕወሓት እየተፈጸመ ያለውን ግድያን ለኮምሽኑ ማሳወቁ ተገልጿል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!