የተጓደሉት 16ቱ የላዕላይ ምክር ቤት አባላት በአዲስ ተተኩ

Prof. Mesfin WoldemariamEthiopia Zare (ቅዳሜ ጥር 24 ቀን 2000 ዓ.ም. February, 2,2008)በወ/ት ብርቱካን የሚመራው ቅንጅት ሥራ አስፈፃሚ በተጓደሉት የላዕላይ ምክር ቤት አባላት ምትክ 16 አዳዲስ አባላትን የመረጠ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም አንዱ መሆናቸውን ከአዲስ አበባ ተደምጧል።

 

ወ/ት ብርቱካን የሚመሩት ቅንጅት ባካሄደው "የላዕላይ ምክር ቤት" ስብሰባ ሥራ አስፈፃሚው "በተጓደሉት 16 የላዕላይ ምክር ቤቱ አባላት ምትክ አዳዲስ አባላትን መርጦ እንዲያሟላ" ተልዕኮ እንደተሰጠው ይታወሳል።

 

ባለፉት ሣምንታት ሥራ አስፈፃሚው በምክር ቤት አባልነት ሊሠሩ የሚችሉ ግለሰቦችን ሲያነጋግር የቆየ መሆኑን የገለፁት ውስጥ አዋቂ ምንጮች ፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም አንዱ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

 

የቀሪዎቹን 15ቱን አዳዲስ የምክር ቤት አባላት ሥም ዝርዝር ለጊዜው ምንጮቹ ለጊዜው መግለጥ ያልወደዱ ቢሆንም፣ እነኚሁ ቀሪዎቹ አባላት በቅንጅት ፓርቲ ውስጥ ንቁና ከፍተኛ ተሳትፎ ታዋቂ መሆናቸውን ግን አልሸሸጉም።

 

የተጓደሉት የ16ቱ የላዕላይ ምክር ቤት አባላት መመረጥ ምክር ቤቱን የተሟላ ከማድረግም አልፎ በድርጅቱ ሕግ መሠረት ሊንቀሳቀስ እንደሚያስችለው ታውቋል።

 

ፕሮፌሠር መስፍን ከቅንጅቱ የመጀመሪያ ውህደት በፊት የነበረው የአራቱ ድርጅቶች የጋራ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የነበሩ ቢሆንም ከመጋቢት 1997 ዓ.ም. ጀምሮ ራሳቸውን ከአመራር አባልነት አግልለው እንደቆዩ አይዘነጋም።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!