Ethiopia Zare (ኀሙስ ኅዳር 4 ቀን 2001 ዓ.ም. November 13, 2008)፦ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪ የነበሩት አቶ ዳንኤል ጎበዜ ከኅዳር 2 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ በገዛ ፈቃዳቸው ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸውንና በምትካቸው አቶ ሊቁ እጅጉ በጊዜያዊነት የተኳቸው መሆኑን ኮሚቴው ለኢትዮጵያ ዛሬ በላከው መግለጫ አስታወቀ።

 

እንደመግለጫው ከሆነ አቶ ዳንኤል ጎበዜ ኮሚቴው ከታቋቋመ ጀምሮ የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪ በመሆን ያገለገሉ መሆኑን ጠቅሶ፣ በቅርቡ በሌላ ድርጅት በተመሳሳይ ኃላፊነት የሚሠሩ በመሆናቸው በራሳቸው ሙሉ ፈቃድ ኃላፊነታቸውን ለቅቀዋል።

 

የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ለሱዳን ተሰጠ የተባለውን የኢትዮጵያን መሬት በተመለከተ እየተከታተለ ለህዝብ ይፋ ለማድረግ የተቋቋመና የድንበሩን ጉዳይ በሚመለከት ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ይታወቃል። (መግለጫውን አስነብበኝ)

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ