Ethiopia Zare (ዓርብ ኅዳር 19 ቀን 2001 ዓ.ም. November 28, 2008)፦ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በራሪ ወረቀቶችን ለማሣተም ገንዘብ ከፍሎ ውጤቱን ሲጠባበቅ ማተሚያ ቤቱ ጽሑፉን ማተም ስለማይችል፤ ገንዘቡን እንዲወስድ መጠየቁን አስታወቀ።

 

የፓርቲው ም/ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ፤ እንደገለጹት በራሪ ወረቀቱን ለማተም ከፈቃጅ አካል ማኅተም አስደርገው እንዲመጡ መጠየቃቸውንና "ቅድመ ምርመራ (ሳንሱር) በሕግ በተከለከለበት ሀገር በሕጋዊ መንገድ ፍቃድ አውጥተን የምንቀሳቀስ ፓርቲ ማተሚያ ቤቱ ከማናውቀው አካል ማኅተም አስደርገን እንድንመጣ ጠይቆናል" ብለዋል።

 

ፓርቲው ቅዳሜ ኅዳር 27 ቀን 2001 ዓ.ም. ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ "ሠላማዊ ትግል" የሚል በራሪ ወረቀት ለማሣተም "ርኾቦት አሣታሚዎች ኃ/የተ/የግል ማኅበር" ለተባለ ማተሚያ ቤት ረቡዕ ኅዳር 17 ቀን 2001 ዓ.ም. የሚያስፈልገውን የሕትመት ዋጋ ከፍለው፣ የሚታተመውን ጽሑፍ አስረክበው ከሄዱ በኋላ፣ በዚያው ዕለት ማምሻውን ተደውሎ ጽሑፉን ማተም ስለማይችሉ ገንዘባቸውን እንዲወስዱ እንደተነገራቸው አስረድተዋል።

 

ማተሚያ ቤቱ ለማተም ፍቃደኛ ያልሆነበትን ምክነንያት ሲጠይቁ፤ ጹሑፉ ላይ ከፈቃጁ አካል ማኅተም ማስደረግ እንዳለባቸው ከመግለጽ ውጭ ፈቃጁ አካል ማን እንደሆነ፣ ማተሚያ ቤቱ በቃል ወይም በጹሑፍ የደረሰው ነገር እንዳለ ጠይቀው ምላሽ አለማግኘታቸውን አስረድተዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ