የአማራ ክልልና አዲስ አበባ ህዝብ ብዛት አከራካሪ ሆኗል

Ethiopia Zare (ዓርብ ኅዳር 26 ቀን 2001 ዓ.ም. December 05, 2008)፦ የኢፌዲሪ የህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን የ1999/2000 ዓ.ም. የኢትዮጵያ የህዝብ ቆጠራ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት 73 ሚሊዮን 918 ሺህ 505 መድረሱን አስታወቀ። የአማራ ክልልና አዲስ አበባ ህዝብ ብዛት አከራካሪ ሆኗል።

 

 

በትናንትናው ዕለት ም/ጠ ሚኒስትር አቶ አዲሱ ለገሰና፣ የስታትስቲክስ ባለሥልጣን ኃላፊ ወ/ሮ ሳሚያ ዘካሪያ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት፤ በ1999/2000 በተካሄደው ቆጠራ በኦሮሚያ 27, 158, 471፣ በአማራ 17,214,056፣ በሶማሌ 4,439,147፣ በትግራይ 4,314,456፣ በአዲስ አበባ 2,738,248፣ በአፋር 1,411,092፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ 670,847፣ በድሬዳዋ 342,827፣ በጋምቤላ 306,916 እና በሐረሪ 183,344 ህዝብ እንደሚኖር ይፋ አድርገዋል።

 

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ77 ሚሊየን ህዝብ በላይ እንደሚኖር አስቀድሞ የተተነበየ ቢሆንም፣ በቆጠራው የ3.2 ሚሊየን ህዝብ ልዩነት መታየቱን ሪፖርቱ ላይ ሠፍሯል።

 

ሪፖርቱ ቀርቦ ከመጽደቁ በፊት፣ አንዳንድ የፓርላማ አባላት እንዲሻሻል የጠየቁት የተለያዩ ጥያቄዎች የነበሩ ሲሆን፣ የአማራ ክልል ህዝብ ቁጥር ከተገመተው በ2 ነጥብ 4 ሚሊየን ህዝብ ቁጥር ቀንሶ መገኘቱ አከራካሪ ሆኗል።

 

የሀገር አቀፍና ክልሎች የህዝብ ብዛት አስቀድሞ ከተገለጸው ትንበያ 3.2 ሚሊየን ህዝብ ቁጥር አንሶ መገኘቱ ባያከራክርም፣ ከዚህ ቁጥር ውስጥ አነስተኛ ቁጥር የአማራ ክልል ይዞ መገኘቱ ሪፖርቱን ጥርጣሬ ላይ እንዲወድቅ እንዳደረጋቸው የፓርላማ አባላቱ ገልጸዋል።

 

ይህንንም በሚመለከት ወ/ሮ ሳሚያ በሰጡት ምላሽ፣ ከተጠቀሰው አጠቃላይ የትንበያ ቁጥር ከፍተኛው 2.4 ሚሊየን የሚሆን የህዝብ ቁጥር በአማራው ክልል ቀንሶ መገኘቱ፣ በነሱም በኩል የማይታመን ሆኖባቸው በድጋሚ እንዲጣራ ማድረጋቸውንና ምንም የተለየ ውጤት ባያገኙም፣ አሁንም በቀጣይ የአማራ ክልል ጉዳይ በልዩ ሁኔታ ታይቶ እንደገና ሊፈተሽ የሚችልበት ሁኔታ እንደሚኖር ጠቁመዋል።

 

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ 2.7 ሚሊየን እንደሆነ መገለጹ እና ለዚህም የተሰጠው ምክንያት፤ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ቀን ቀን ትርምስ ቢፈጠርም ማታ ማታ በከተማው ዳር ላይ በሚገኙ ሌላ ከተሞች የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በመደባለቃቸው እንጂ፣ የከተማው ነዋሪ የተጠቀሰው ቁጥር ያህል ነው መባሉ፣ ከውጭ ሀገር የተቀዳ ከመሆኑ በስተቀር ካለው ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር አንፃር ነዋሪው ከተማ ወጥቶ እንደማይኖር እየታወቀ፣ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በማይገልጽ አኳኋን ሪፖርት ማቅረቡ አግባብ እንዳልሆነ ተተችቷል።

 

በሌላም በኩል የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ ከሙስሊሙ እምነት ተከታዮች ቁጥር በልጦ መገኘቱ፤ በእስልምና ክብረ በዓላት ላይ በስታዲየም የሚገኘውን እና በክርስትና በዓላት ላይ የሚገኘውን ምዕመናን ቁጥር ያላገናዘበ እንደሆነ በመግለጽ፣ የሙስሊሙ እምነት ተከታይ ከክርስቲያን ማነሱ ሪፖርቱን ጥርጣሬ ላይ እንዲጥሉት እንዳደረጋቸው አንድ የኢህአዴግ አጋር ድርጅት አባል ተናግረዋል።

 

በተሰጠው ምላሽ የተነሱት ጥያቄዎች፣ ከአማራ ክልል በስተቀር ግምት የማይሰጣቸው መሆናቸው ተገልፆ ሪፖርቱ እንዲጸድቅ ተደርጓል።

 

ሀገር አቀፍ የህዝብ ብዛት በኃይማኖት

የኃይማኖት ዓይነት

1999

1987

ብዛት

በመቶኛ

ብዛት

በመቶኛ

ጠቅላላ

73,918,505

100.0

53,130,781

100.0

ኦርቶዶክስ

32,138,126

43.5

26,877,660

50.6

ፕሮቴስታንት

13,746,787

18.6

5,405,107

10.2

ካቶሊክ

536,827

0.7

459,548

0.9

የክርስቲያን ድምር

46,421,740

62.8

32,742,315

61.6

ሙስሊም

25,045,550

33.9

17,412,431

32.8

ባህላዊ

1,957,944

2.7

2,455,053

4.6

ሌሎች

471,861

0.6

478,226

0.9

መልስ ያልሰጡ

 

 

42,756

0.1

 

ሀገር አቀፍ የህዝብ ብዛት በፆታ

 

 

ክልል

ፆታ

ድምር

ወንድ

ሴት

ቁጥር

በመቶኛ

ቁጥር

በመቶኛ

ቁጥር

በመቶኛ

ሀገር አቀፍ

73,918,505

100.0

37,296,657

50.5

36,621,848

49.5

ትግራይ

4,321,456

100.0

2,124,853

49.3

2,189,603

50.7

አፋር

1,411,092

100.0

786,338

55.7

624,754

44.3

አማራ

17,214,056

100.0

8,636,875

50.2

8,577,181

49.8

ኦሮምያ

27,158,471

100.0

13,676,159

50.4

13,482,312

49.6

ሶማሌ

4,439,147

100.0

2,5468,784

55.6

1,970,363

44.4

ቤንሻንጉል-ጉሙዝ

670,847

100.0

340,378

50.7

330,469

49.3

...

15,042,531

100.0

7,482,051

49.7

7,560,480

50.3

ጋምቤላ

306,916

100.0

159,679

52.0

147,237

48.0

ሐረሪ

183,344

100.0

92,258

50.3

91,086

49.7

አዲስ አበባ

2,738,248

100.0

1,304,518

47.6

1,433,730

52.4

ድሬዳዋ

34,827

100.0

171,930

50.2

170,897

49.8

ልዩ ቆጠራ አካባቢ

96,570

100.0

52,834

54.7

43,736

45.3

 

 

በኢትዮጵያ በ1999/2000 የተካሄደውን ቆጠራ ጨምሮ፣ ሦስት ጊዜ የህዝብና ቤት ቆጠራ የተካሄደ ሲሆን፣ በ1976 በተካሄደው የመጀመሪያው ቆጠራ የሀገሪቱ የህዝብ ብዛት 42,616,876 እንደነበርና ከ11 ዓመታት በኋላ በ1987 በተካሄደው ቆጠራ የህዝብ ብዛቱ በ11 ሚሊየን በመጨመር 53,477,265 ደርሶ ነበር።

 

የ1999/2000 ቆጠራ ካለፈው ቆጠራ ጋር ሲነፃፀር፣ በ20.4 ሚሊየን ህዝብ ዕድገት እንደተመዘገበ የገለፀው የኮሚሽኑ ሪፖርት፣ የፆታ ስብጥሩ ተቀራራቢ በመሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የወንዶች ብዛት 37,296,657 የሴቶች ደግሞ 36,621,848 መሆኑን ይፋ አድርጓል።

 

በዚህም መሠረት የፆታ ስብጥሩ በመቶኛ የወንዶቹ 50.5 በመቶ፣ የሴቶቹ 49.5 በመቶ መሆኑን አስታውቋል።

 

በቆጠራው ላይ 100,000 የሚሆኑ የመስክ ሥራ አስተባባሪዎች፣ ቆጣሪዎችና ተቆጣጣሪዎች መሳተፋቸውን ያስታወቀው የኮሚሽኑ ሪፖርት፣ በቆጠራው ወቅት ቤተሰቦች ሳይቆጠሩ እንዳይዘለሉ ለማጣራት የየክልሎቹ የቆጠራ ኮሚሽኖች እንዲያረጋግጡ ተደርጓል።

 

የኮሚሽኑ ሪፖርት እንዳመለከተው በኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ህዝብ ውስጥ 83.8 በመቶው ወይም 61,962,335 የሚሆነው በገጠር የሚኖር ሲሆን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ በከተማ የሚኖረው ህዝብ 16.2 ወይም 11, 956,170 ነው።

 

ከፍተኛ የገጠር ነዋሪ ካላቸው መሃከልም የኦሮሚያ፣ የአማራና የደቡብ ክልሎች ከህዝባቸው መሃከል ከ87-90 በመቶው በገጠር እንደሚኖር የቆጠራው ውጤት ያሳያል።

 

በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ ላይ ካሉ ከተሞች መካከልም የኦሮሚያዋ ቡራዩ፣ የደቡብ ክልል መዲና ሐዋሳ፣ የትግራይ ክልል መዲና መቀሌ፣ የሶማሌ ክልል መዲና ጅጅጋ፣ የጋምቤላ ከተማና ሻሸመኔ ከተማ ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ጭማሪ የታየባቸው ተብለው ተጠቅሰዋል።

 

የቆጠራ መረጃው እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ህዝብ ማለትም 38,468,083 ያህሉ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ነው። ከዚህ ውስጥ ደግሞ ከ5 ዓመት በታች የሆኑት ሕፃናት 11 ሚሊየን የሚደርስ ሲሆን፣ ከ75 ዓመት በላይ የሚሆኑት ደግሞ 846,359 ይሆናል።

 

የህዝብ ብዛት በብሔር ሲገለፅ ኦሮሞ 34.5 በመቶ፣ አማራ 26.9 በመቶ፣ ሶማሌ 6.2 በመቶ፣ ትግሬ 6.1 በመቶ፣ ሲዳማ 4 በመቶ፣ ወላይታ 2.3 በመቶ በመሆን ከአንደኛ እስከ 7ኛ ድረስ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

 

በኃይማኖት በኩልም፣ ከአጠቃላይ ህዝብ 62.8 በመቶ ወይም 46,421,740 ያህሉ የክርስትና እምነት 33.9 በመቶው ወይም 25,045,550 ያህሉ የእስልምና እምነት ተከታይ፣ ሌሎች ደግሞ 3.3 በመቶ መሆናቸው የቆጠራው ውጤት ያመለክታል።

 

ይህም ከ1987 ጋር ሲወዳደር የክርስትና እምነት ተከታዮች በ1.2 በመቶ፣ የእስልምና እምነት ተከታዮች በ1.1 በመቶ ሲጨምሩ፣ በጥቅል ሲታይም የኦርቶደክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች 43.5 በመቶ፣ የእስልምና እምነት ተከታዮች 33.9 በመቶ፣ ፕሮቴስታንት 18.6 በመቶ መሆናቸው የቆጠራው ውጤት ዝርዝር ያሳያል።

 

ቆጠራው በመላው ሀገሪቱ በሁለት የተለያዩ ጊዜያት፣ በግንቦት 1999 ዓ.ም. እና ኅዳር 2000 ዓ.ም. ላይ ሲካሄድ፣ በሶማሌ ክልል ራሶ በተባለ አካባቢ፣ የአካባቢው ህዝብ ተወካዮች ከቴክኒካዊ አሠራሩ ውጪ የሆነ ጥያቄ በማቅረባቸው በቆጠራው አለመካተታቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ