”በወያኔ ምርጫ ማናቸውም ተቀዋሚዎች መሳተፍ የለባቸውም” አቶ አዛለ ደስታ

”ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ምርጫ መገባት አለበት" ተክለሚካኤል አበበ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ኅዳር 30 ቀን 2001 ዓ.ም. December 9, 2008)፦ በመጪው 2002 ዓ.ም. (2010 እ.ኤ.አ.) ምርጫ በሀገር ቤት የሚገኙ የተቃዋሚ ኃይሎች ምን ማድረግ ይገባቸዋል ከሚል ሃሳብ በመነሳት የመጀመሪያው ህዝባዊ ስብሰባ በቫንኩቨር ካናዳ ቅዳሜ ዲሴምበር 13 ቀን 2008 እ.ኤ.አ. እንደሚካሄድ ተለጸ።

 

በስብሰባው ላይ ሁለት ተናጋሪዎች የሚቀርቡ ሲሆን፣ አቶ አዛለ ደስታ ”በወያኔ ምርጫ ማናቸውም ተቀዋሚዎች መሳተፍ የለባቸውም” በሚል ርዕስ ጽሑፍ እንደሚያቀርቡ የታወቀ ሲሆን፤ የቀድሞው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፕሬዝዳንት የነበረው ተክለሚካኤል አበበ ደግሞ ”ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ምርጫ መገባት አለበት” በሚል ጽሑፍ የሚያዘጋጅ መሆኑ ተገልጿል።

 

በውይይቱ ላይ

 

  • በዚህ ”ምርጫ” በሀገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል? ምንስ አቋም ሊይዙ ይገባል?
  • በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ድርሻና ተጽዕኖ ምን ድረስ ነው?
  • ወደ ”ምርጫ” መገባቱ የሚያመጣው አወንታዊ እና አሉታዊ ገጽታዎች ምንድን ናቸው?
  • ካለፈው ”ምርጫ” ምን ተምረናል? ...

 

በእነዚህና መሰል ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዩች ላይ ውይይት እንደሚደረግና ሀገር ቤት ለሚገኙም ሆኑ በውጭ ለሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ጠቃሚ ሃሳብና የመረጃ አስተዋጽዖ ያበረክታል በሚል ተከታታይ የውይይትና የክርክር መድረኮችን እንደሚዘጋጁ ታውቋል።

 

የውይይቱ ቦታ፦ ሞዛይክ 1720 Grant st. Vancouver (Commercial Dr and grant st.)

 

ቅዳሜ ዲሴምበር 13 ቀን 2008 እ.ኤ.አ. ከ4 PM ሰዓት ጀምሮ መሆኑንና በስፍራው በመገኘትም ሆነ በሚድያዎች በመከታተል ያለዎትን ሃሳብ እንዲያካፍሉና የሌሎችንም ሃሳብ እንዲጋሩ አዘጋጆቹ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ