20210302 adwa

Ethiopia Zare (ዓርብ የካቲት 7 ቀን 2000 ዓ.ም. February 15,2008)፦ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የፎቶ ጋዜጠኞች ማኅበር በዚህ ሣምንት መቋቋሙ ታወቀ። የማኅበሩ መጠሪያ ስም "ብሔራዊ የፎቶ ጋዜጠኞች ማኅበር" ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱ አቶ ቢንያም መንገሻ መሆናቸው ታውቋል።

ማኅበሩ የተቋቋመው በአምስት የፎቶግራፍ ባለሙያዎች አማካኝነት ሲሆን፣ ፍትህ ሚኒስቴር የካቲት 3 ቀን 2000 ዓ.ም የእውቅና ሠርቲፊኬት (የምስክር ወረቀት) ሰጥቶታል።

የማኅበሩ መሥራች አባላት ፕሬዝዳንቱና ፕሮፌሽናል የፎቶግራፍ ባለሙያ የሆኑት አቶ ቢንያም መንገሻ፣ ወ/ሮ አሌኒ ኃ/ሚካኤል የኤ.ቢ.ቢ.አይ. ዊክሊ ጋዜጣ ፎቶግራፈር፣ አቶ መስፍን ሠለሞን የካፒታል ጋዜጣ ፎቶግራፈር፣ አቶ ናሆም ተስፋዬ የሪፖርተር ጋዜጣ ፎቶግራፈር፣ እና አቶ አዲስ በለጠ የሥራና ከተማ ልማት ቢሮ ፎቶግራፈር መሆናቸው ታውቋል።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!