ውይይት ለሰላምና ለጋራ አላማ በኢትዮጵያ
ታላቅ የስብሰባ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ
Ethiopia Zare (ረቡዕ መጋቢት 16 ቀን 2001 ዓ.ም. March 25, 2009)፦ ባለፈው ዓመት መጨረሻ የተጀመረውና በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በየሶስት ወሩ የሚደረገው የውይይት መድረክ ቀጣይ የውይይት ርእሶችን በማዘጋጀት ለሁለተኛ ጊዜ ታላቅ የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱ ተገለጸ። የመጀመሪያው ውይይት “ከፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የፕራዜዳንታዊ ውድድር ኢትዮጵያዊያን ምን ልንማር እንችላለን?” የሚል ነበረ ሲሆን በስብሰባው ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸው እንደነበር አይዘነጋም።
ለሁለተኛ ጊዜ በማርች 29, 2009 በታቀደው ውይይት በሶስት ርእሰ ጉዳዮች ላይ ተጋባዥ ተናጋሪዎች ያዘጋጇቸው ትናታዊ ጽሁፎች እንደሚቀርቡ ለማወቅ ችለናል።
በውይይቱ ላይ ‘የፖለቲካ ፓርቲዎች ታሪክና ሂደት’ በሚል ርእስ ዶ/ር ሹመት ሲሻኝ ያዘጋጁትን ጽሁፍ ለውይይት የሚያቀርቡ ሲሆን ዶ/ር አክሊሉ ኃብቴ ደግሞ ‘የኢትዮጵያን የትምህርት ፖሊሲ እንመርምር’ ሲሉ ያዘጋጁትን ይዘው ይቀርባሉ። የቀድሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ም/ቤት ፕሬዝዳንት የነበረውና በአሁኑ ሰአት ቫንኩቨር ካናዳ ውስጥ የህግ ትምህርቱን እየተከታተለ የሚገኘው ተክለሚካኤል አበበ ደግሞ ‘ወጣቶች ከኢትዮጵያ ምሁራን ምን ይጠብቃሉ’ በሚለው ጥያቄ ላይ ያተኮረ ጽሁፍ ለተሳታፊዎቹ እንደሚያቀርብ ተገልጿል። የውይይቱን መድረክ የሚመሩት ዶ/ር ብርሃኑ መንግስቱ እንደሚሆኑ ለመረዳት ችለናል።
የውይይቱ ቦታ፦
Johns Hopkins University
1740 Massachusetts Avenue, N.W.
Washington, D.C.
Sunday March 29, 2009
2፡00 P.M. - 6፡00 P.M.
በአካባቢው ያላችሁ ነዋሪዎች በቦታው በመገኘት የውይይቱ ተካፋይ እንድትሆኑ አዘጋጆቹ ግብዣቸውን ያቀርባሉ።



