Ethiopia Zare (ማክሰኞ መጋቢት 22 ቀን 2001 ዓ.ም. March 31, 2009)፦ በአዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሴት ተማሪዎች እየጠፉ መሆኑ እየተገለጸ ሲሆን፣ ፖሊስና የትምህርት ቤቶቹ ኃላፊዎች ጉዳዩን ሐሰት ነው በማለት እያስተባበሉ ይገኛሉ።

 

በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ በእውቀት ምንጭ፣ በብሉ በርድ፣ ገላን ቁጥር ሁለት እና ሌሎች ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች እየተሰረቁ እየጠፉ መሆኑ በሰፊው እየተወራ ቢሆንም ፖሊስ ይህን አስመልክቶ የገለጸው ነገር የለም። የትምህርት ቤቶቹም አስተዳዳሪዎች ጉዳዩ ከወሬ ባለፈ በተጨባጭ የደረሱበት ነገር እንደሌለ እየገለጹ ነው።

 

በሌላ በኩል የገላን ቁጥር ሁለት ትምህርት ቤት አንድ መምህርት የእነሱን ትምህርት ቤት በሚመለከት ሲገልጹ፤ ከየካቲት ወር ጀምሮ አራት ሴት ተማሪዎች መጥፋታቸውንና ይህንንም ትምህርት ቤቱ ለፖሊስ ሪፖርት ማድረጉን ተናግረዋል። ነገር ግን ፖሊስም ቢሆን ክትትል ማድረግ የጀመረው ዘግይቶና በሁለቱ ሴት ተማሪዎች መጥፋት ላይ አተኩሮ ብቻ መሆኑን አስረድተዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ