20210302 adwa

ፍርዱ አግባብ አይደለም ያሉ መምህራን ታፈሱ

‘ውሳኔው ኢ-ፍትሀዊ ነው’ አቶ ገሞራው ካሣ

Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 19 ቀን 2000 ዓ.ም. February 27,2008)፦ በ1941 ዓ.ም. የተቋቋመውና ቀደም ሲል በዶ/ር ታዬ ወልደሰማያት ይመራ የነበረው አንጋፋው የመምህራን ማህበር ከ15 ዓመታት የፍርድ ሙግት በኋላ በ1985 ዓ.ም. ለተመሰረተውና በኢህአዴግ ተቀጥላ ለሆነው ቡድን የተወሰነ መሆኑን ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ ጠቆመ።

 

በሚያዚያ ወር 1985 ዓ.ም. የማኅበሩ የይገባኛል ጥያቄ ፋይል በፍርድ ቤት ተከፍቶ ክርክር ሲደረግበት ቆይቷል። በሂደቱም ሁለቱም ቡድን በይግባኝ ሲሸናነፉ ቆይተዋል።

 

በመጨረሻም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥር 25 ቀን 2000 ዓ.ም ቀደም ሲል በዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያት አሁን ደግሞ በአቶ ገሞራው ካሳ ሚመራው መምህራን ማኅበር ላይ ወስኖ በአቶ አንተዬ ለሚመራው ማኅበር ቢሮውን እንዲያስረክቡ አዟል።

 

ውሳኔውን አስመልክቶ አቶ ገሞራው ካሳ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ የሚመሩት ማኅበር በ1941 ዓ.ም. የተቋቋመና በፍትህ ሚኒስቴር፤ በአገሪቷ 25ኛ ማኅበር ሆኖ የተመዘገበ እያለ፣ በ1985 ዓ.ም በተፈጠረ አለመግባባት ከመካከላቸው ለወጡ ቡድኖችና 161ኛ ማኅበር ሆነው ለተመዘገቡት ቡድኖች ውሳኔ መስጠቱ ፍርዱን ፍትሃዊ እንደማያደርገው የገለጹ ሲሆን፣ እስከ ሰበር ድረስ ቀርበው እንደሚከራከሩ ተናግረዋል።

 

ውሳኔውን የተቃወሙ መምህራን ላልመረጥነው ማኅበር ንብረታችንን አናስረክብም በማለት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ለማስገባት በሚሯሯጡበት ሰዓት የደህንነት ሠራተኞች ወደ ሰባት የሚጠጉ መምህራንን አስረውና አስፈራርተው እንደለቀቋቸው አቶ ገሞራው ካሣ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ለሁለት ተከፍሎ የይገባኛል ጥያቄ በማንሳት የማህበሩ ጽ/ቤት ለረጅም አመታት ታሽጎ እንደነበር ይታወሳል።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!