በርካታ ሰዎችና ሁለት ፖሊሶች ቆስለዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሚያዝያ 24 ቀን 2001 ዓ.ም. May 2, 2009)፦ በደቡብ ክልል ጊዶሌ ከተማ በግጦሽ መሬት ምክንያት በመጣላታቸው በርካታ ሰዎችና ሁለት ፖሊሶች ቆሰሉ።

 

ከአራት ወራት በፊት ተመሳሳይ ግጭት ተነስቶ “አሸለሌ” እና “ቀያማ” የተባሉ ሁለት ቀበሌዎች የተቃጠሉበት የደቡብ ክልል ጊዶሌ ከተማ ባለፈው ሣምንትም በድጋሚ ግጭት መፈጠሩን ምንጮች ጠቁመዋል።

 

ግጭቱ ሊቀሰቀስ የቻለው ባለፈው ሣምንት በደቡብ ክልል ከጊዶሌ ከተማ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ “አቡሎ” በተባለች ቀበሌ የሚገኙ አርሶ አደሮች የደራሼ አርሶ አደሮች ወደሚገኙበት አካባቢ የግጦሽ ሣር ከብቶቻቸውን ለማስጋጥ በማስገባታቸው ነው።

 

ከብቶቹ የግጦሽ ሣር ወደሚገኝበት ቦታ ገብተው እየጋጡ ባሉበት ወቅት ያንን ያዩ የኮንሶ አርሶ አደሮች በመቆጣታቸው አነስተኛ ፀብ የተፈጠረ ሲሆን፣ ይኸው ፀብ ተጋግሎ እርስ በእርሳቸው ተቋስለዋል።

 

ግጭቱን ለማብረድ ወደ ስፍራው የደረሰው የጊዶሌ ከተማ የፖሊስ ኃይል ወደ ውስጥ ዘልቆ እንዳይገባ ከአርሶ አደሮቹ ተኩስ የተከፈተበት ሲሆን፣ ሁለት ፖሊሶች በድንጋይና በጥይት ተደብድበው ሲቆስሉ ሌሎቹ ወደኋላ በማፈግፈግ ማምለጣቸው ታውቋል።

 

በዚሁ ከተማ ከአራት ወራ በፊት ተመሳሳይ ግጭት ተነስቶ “አሸለሌ” እና “ቀያማ” የተባሉ ሁለት ቀበሌዎች መቃጠላቸውን ምንጮቻችን ጠቁመዋል። በአሁኑ ሰዓትም ግጭቱን ለማብረድ የፖሊስ ኃይል ወደ ስፍራው መጓዙ ታውቋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ