የአልባኒያዊቷ ተወዳዳሪ ስሟ ኢትዮጵያዊ ነው፣ ‘ኬይሲ ቶላ” ትባላለች

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 8 ቀን 2001 ዓ.ም. May 16, 2009)፦ ዛሬ ማምሻውን በተጠናቀቀው “ዮሮቪዥን” በመባል በሚታወቀውና በሞስኮ በተካሄደው 54ኛው የአውሮፓ ሀገሮች የሙዚቃ ውድድር ኖርዌይ አሸናፊ ሆነች። “ፌሪቴይልስ” በተሰኘው ዘፈኑ ኖርዌይን አሸናፊ እንድትሆን ያደረጋት የ23 ዓመቱ አሌክሳንደር ሪባክ የተሰኘው ድምፃዊ ነው።

 

አሌክሳንደር ሪባክ ሜይ 13 ቀን 1986 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ.) በአሁኑ ጊዜ ቤላሩስ እየተባለች በምትጠራዋ የቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረት የተወለደ ሲሆን፣ የኖርዌይ ዜግነት ያለው ድምፃዊ፣ የቫዮሊን ተጫዋች፣ የሙዚቃ አቀናባሪና የፊልም ተዋናይ ነው።

 

54ኛው ዩሮቪዥን የሙዚቃ ውድድር የተካሄደው በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ ሲሆን፣ የማጣሪያው ውድድር ግንቦት 4 ቀን 2001 ዓ.ም. (May 12, 2009) እና ግንቦት 6 ቀን 2001 ዓ.ም. (May 14, 2009) ተካሂዶ ነበር። የፍፃሜው ውድድር ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2001 ዓ.ም. (May 16, 2009) ሞስኮ በሚገኘው የቤት ውስጥ ኦሎምፒክ አሬና ውስጥ ነበር የተካሄደው።

 

በዚህ ውድድር ላይ 42 የአውሮፓ ሀገራት የተካፈሉ ሲሆን፣ የውድድሩ አሸናፊ የተለየው 50 በመቶ በዳኞች ድምፅ እና 50 በመቶ ደግሞ በቴሌፎን ድምፅ (televoting) ነበር።

 

በዚህ የዩሮቪዥን የሙዚቃ ውድድር የአውሮፓ ሀገራት የየራሳቸውን ሀገር ባህል፣ ቋንቋ፣ ወግ፣ ... ለመላው አውሮፓ ሀገራትና ለመላው ዓለም የሚያስተዋውቁበት እንደሆነ ይታወቃል። በዚህ በ54ኛው የዩሮቪዥን የሙዚቃ ውድድር ላይም ይህ ሁኔታ የተንፀባረቀበት ነበር።

 

የመጨረሻው የቴሌፎን ድምፅ አሰጣጡ በተካሄደበት ወቅት በመላው አውሮፓና በዓለም በተላለፈው በዚሁ የሙዚቃ ውድድር የቀጥታ ስርጭት ላይ ከአስተዋዋቂዎቹ አንዷ፤ “ሩሲያውያን በቀን 24 ሰዓት ጠጪዎች መሆናችን ይነገራል - ይህ ሐሰት ነው፤ በሩሲያ የበጋ ወራት በረዶ እንደሚዘንብ ይነገራል - ይህም ሐሰት ነው፤ ሩሲያን የሚመራትና የሚገዛት ኬ.ጂ.ቢ. ነው ይባላል - ይህም ቢሆን ፍፁም ሐሰት ነው!፣ ...” በማለት ሩሲያና ህዝቧ የሚተቹባቸውን ነጥቦች አስተባብላለች።

 

ይኸው በሞስኮ የተካሄደው “ዩሮቪዥን 2009” ቢያንስ 10 ሚሊዮን የስዊድን ክሮነር (አንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር) እንደፈጀ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

 

በዚህ ውድድር ላይ ከተካፈሉት ሀገራት ውስጥ አልባንያ ስትሆን፣ ሀገሪቱን በመወከል የተሳተፈችው “ኬይሲ ቶላ” (Kejsi Tola) የምትባል ዘፋኝ ነች። በአማርኛ ቋንቋ “ኬይሲ” ማለት ግብሩ የሠይጣን የሆነ፣ ለመጥፎ ሥራዎች በሙሉ የተፋጠነ ሰው፣ ጨካኝ፣ ክፉ ሰው የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን፣ የቤተሰብዋ መጠሪያ ስም ደግሞ “ቶላ” ተብሎ ሊነበብ ይችላል። “ቶላ” የሚለው ስም ደግሞ የኦሮሞ ስም ሲሆን፣ ትርጉሙም ሆነ፣ ይሆንልናል፣ ይደረግልኛል፣ ተደረገ፣ ተደረገልኝ፣ ... የሚል ትርጉም እንዳለው ይታወቃል።

 

ዛሬ በሥልጣን ላይ የሚገኘው የኢህአዲግ መንግሥት ከደርግ ጋር ሲያደርገው በነበረው ጦርነት ወቅት የአልባንያ ሶሻሊስት ተከታይ እንደነበር አይዘነጋም። በወቅቱ አልባኒያ “የተዘጋ ቤተክርስቲያን” የሚል መጠሪያ እንደነበራት አይዘነጋም።

 

በ2008 እ.ኤ.አ. በሰርቢያ የተካሄደውን 53ኛውን የዩሮቪዥን የሙዚቃ ፌስቲቫል ሩሲያ በማሸነፏ ምክንያት የ2009ኙን ለማዘጋጀት በቅታለች። በዚሁ መሠረት በሚቀጥለው የአውሮፓውያን ዓመት 2010 ዓ.ም. የሚካሄደውንና 55ኛውን የዩሮቪዥን የሙዚቃ ውድድር የምታዘጋጀው ኖርዌይ ትሆናለች።

 

የዩሮቪዥን 2009 አሸናፊ የሆነው የአሌክሳንደር ባሪክ “ፌሪቴይልስ” የተሰኘው ዘፈን ግጥም የሚከተለው ነው።

 

Years ago, when I was younger

I kind a liked, a girl I knew

She was mine and we were sweet hearts

That was then, but then it's true

I'm in love with a fairytale

Even though it hurts

Cause I don't care if I lose my mind,

I'm already cursed

 

Every day we started fighting

Every night we fell in love

No one else could make me sadder

But no one else could lift me high above

I don't know what I was doing

When suddenly we fell apart

Nowadays I cannot find her

But when I do we'll get a brand new start

I'm in love with a fairytale

Even though it hurts

Cause I don't care if I lose my mind,

I'm already cursed

 

She's a fairytale yeah

Even though it hurts

cause I don't care if I lose my mind,

I'm already cursed

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ