Ethiopia Zare (ረቡዕ ግንቦት 12 ቀን 2001 ዓ.ም. May 20, 2009)፦ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ባለፉት ጊዜያት በማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት ለድርጅቱና ለህዝብ ይፋ በሆነው ሰነድ ላይ በመነሳት ለሁለት ቀናት ስብሰባ በማካሄድ እልባት ላይ መድረሱን የድርጀቱ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊና ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።

 

በውይይቱ ላይ ከመድረክ ለዲሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ (መድረክ) ጋር ድርጅቱ ያለውን ግንኙነት፣ የአሠራር ድክመቶችና አምባገነንነት ላይ ያተኮሩትን የመወያያ ሃሳቦች በጽሑፍ የቀረቡ ሲሆን፣ በተነሱት ሰነዶች ላይ በመመርኮዝ ውሳኔ መሰጠቱን ለመረዳት ችለናል። በተለይ ከመድረክ ጋር ያለውን ግንኙነት በሚመለከት ብሔራዊ ምክር ቤቱ በሰጠው ውሳኔ መሰረት ምንም አይነት እድገት ባለመኖሩ በሁለት ሣምንት ውስጥ ሪፖርቱ እንዲቀርብ መወሰኑን ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

 

በድርጅቱ አሠራር ላይ የተነሱትን ድክመቶችና ጠንካራ ጎኖች በማንሳት በተለይ የድክመቶቹ ምክንያቶች በተባሉ ነጥቦች ላይ በተለይም የበጀት፣ የሰው ኃይል፣ በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ ውዥንብሮችና የሊቀመንበሯ ወ/ት ብርቱካን መታሰር ያስከተሉትን ችግሮች በሚመለከት ሰፊ ውይይት መደረጉን አክለው ገልጸዋል።

 

ከአምባገነንነት ጋር በተያያዘ የተነሳውን ጉዳይም ከምን አንጻር እንደታየና መስተካከል ስላለበት ጠቅላላ ሁናቴ በሚመለከት ምክር ቤቱ የተነጋገረበት ከመሆኑም በላይ በአባላቶች የቀረቡት ጥቆማዎች በጠቅላላ ለድርጅቱ የዲሞክራሲያዊ አካሄድ ገንቢ ከመሆናቸውም በላይ አብዛኞቹ የተከሰቱ ችግሮች ቢሆኑም አንዳንዶቹ የተፈጠሩትን ችግሮች ካለመረዳት መሆናቸውን የድርጅቱ ም/ሊቀመንበርና ቃል አቀባይ ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገልጸዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ