የምርጫ ቦርድ ምላሽ ነገ ይጠበቃል 

Ethiopia Zare (ኀሙስ የካቲት 27 ቀን 2000 ዓ.ም. March 06,2008) ከእስር የተፈቱት የቀድሞው ቅንጅት //ሊቀመንበር / ብርቱካን ሚደቅሳን ጨምሮ 12 አባላት አዲስ ፓርቲ ሊያቋቁሙ መሆኑን በመግለፅ ፊርማ ለማሰባሰብ የሚያስችላቸውን የድጋፍ ደብዳቤ እንዲሰጣቸው በትናንትናው ዕለት ለምርጫ ቦርድ ያመለከቱ ሲሆን፣ ፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም ለአዲሱ ፓርቲ ፊርማ ለማሰባሰብ ወደ አማራ ክልል እንደሚጓዙ ዛሬ ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ ጠቆመ። 

በትናንትናው ዕለት አቶሉነህ ኢዩኤል ምርጫ ቦርድ ተገኝተው የአዲሱን ፓርቲ ማመልከቻ ለቦርዱ ያቀረቡ ሲሆን፣ ምላሽ ለማግኘት ለነገ ቀጠሮ እንደተሰጣቸውም ተውቋል።

አስራ ሁለት አባላት በጋራ ፈርመው ለቦርዱ ያቀረቡት ደብዳቤ እንደሚያስረዳውም፤ አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም የሚፈልጉ በመሆናቸው አንድ ሺህ 500 ፊርማ ለማሰባሰብ በየክፍለ ሃገሩ ለሚንቀሳቀሱ ሰዎች የፊርማ ማሰባሰቢያ ፎርምና የድጋፍ ደብዳቤ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም በፊርማቸው ጥያቄውን ያቀረቡት፤ / ብርቱካን ሚደቅሣ፣ አቶ ሙሉነህ ኢዩኤል፣ / ግዛቸው ሽፈራው፣ / ኃይሉ አርኣያ፣ / ያቆብ /ማርያም፣ አቶ ተመስገን ዘውዴ፣ / ሽመልስ /ፃድቅ፣ አቶ አክሉ ግርጌ፣ አቶለሺ ጠና አቶ መሐመድሊ፣ አቶ አስራት ጣሴ እና አቶ ዲባባ አምኔሳ ናቸው።

በተጨማሪም ፊርማ ለማሰባሰብ እንዲችሉ 48 አባላት የድጋፍ ደብዳቤ እንዲፃፍላቸው ተጠይቋል።  ከእነዚህ ውስጥ ፕሮፌሠር መስፍን /ማርያም የሚገኙበት ሲሆን፣ ፊርማውን የሚያሰባስቡት ወደ አማራ ክልል ተጉዘው እንደሆነ ታውቋል።

በተያያዘም ባለፈውምንት ቅዳሜ የላዕላይ ምክር ቤቱ አባላት ተሰብስበው ፓርቲው በአዲስ ስም መመዝገብ አለበት ሲሉ የውሳኔ ሃሳብ ያሳለፉ ሲሆን፣ በተጓደሉ የሥራ አስፈጻሚ አባላት ምትክም መምረጣቸውን መዘገባችን ይታወሳልቀደም ሲል የሥራ አስፈፃሚ አባላት በነበሩትአቶ ልደቱ አያሌው፣ በአቶ ሙሼ ሰሙ፣ በአቶ አብዱረህማን አሕመዲን፣ በአቶ መስፍን አያሌው እና በወ/ ሙሉዓለም ታረቀኝ ምትክ ሌላ አምስት አስፈጻሚ ተመርጧል። የተተኩት ተመራጮች ዶ/ ኃይሉ አርኣያ፣ አቶ ክፍሌ ጥግነህ፣ አቶ አስራት ጣሴ፣ አቶ መሐመድ እና አቶ ተመስገን ዘውዴ ናቸው።

በተጨማሪም አስፈፃሚው፣ አዲሱን ፓርቲ የማስመዝገቡን ሂደት የሚከታተል ንዑስ ኮሚቴ፣ የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ፣ የፓርቲውን ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ክለሳ የሚያደርግ ኮሜቴና የፓርቲውን ስያሜ በሚመለከት በአገር ውስጥና በውጭ አገር ከሚገኙ አባላትና ደጋፊዎች አማራጭ የሚያሰባስብ ኮሚቴ አቋቁሞ በአንድ ወር ውስጥ የፓርቲውንጋዊነት ለመያዝቅድ ይዞ ስብሰባው መበተኑ ታውቋል።

በሌላ በኩል / ብርቱካን ሚደቅሣ ባለፈው ማክሰኞ ወደ አዋሣ ተጉዘው በቅንጅት ስም ተመርጠው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ከገቡ 23 አባላት ጋር መወያታቸውን መዘገባችን አይዘነጋም። በስብሰባው ላይም አባላቱ ለሊቀመንበሯ በርካታ ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን ከጥያቄዎቹ መካከልም ቅንጅቱ በምን መንገድ መቀጠል ይችላል? የሚል ነበር። ቅንጅት ስሙን ቀይሮ በአዲስ ስም በመመዝገብ እንዲቀጥል መወሰኑን ይህንንም አስፈጻሚውራውን በኮሚቴ ተከፋፍሎ በአጭር ጊዜጋዊነቱን ለማግኘት እቅድ እንደተያዘ ገልጸውላቸዋል።   

ቅንጅት ስሙን ይቀይር እንጂ ዓላማው የማይሞትና የሚቀጥል መሆኑን / ብርቱካን ለአባላቱ መግለጻቸውንና በቅርብ ጊዜም የፓርቲውጋዊነት ተረጋግጦ ሁሉም የተዘጉ ቢሮዎች እንደሚከፈቱ ቃል ገብተው ስብሰባው መበተኑን በኢትዮጵያ ዛሬ በዕለቱ (ማክሰኞ ዕለት) መዘገቡ አይዘነጋም።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ