Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 17 ቀን 2001 ዓ.ም. July 24, 2009)፦ ”ድሃን ማቆር” እየተባለ የሚነገርለት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ በመጪው ዓመት ሊቋረጥ መሆኑ ታውቀ። የባንክ ምንጮች እንደገለጹት መንግሥት በአጋጠመው የገንዘብ ቀውስ ምክንያት ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉት የክልል ከተሞች የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ይቋረጣል።

 

የኅብረተሰቡ የመክፈል አቅም በተመናመነበት በአሁኑ ወቅት በየክልሎቹ ተሠርተው የተቀመጡ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ገዢ ያጡ ሲሆን፣ ባንኮች ለቤቶች ልማት ኤጀንሲ ያበደረውን ገንዘብ በወቅት ማግኘት እንዳልቻለ ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል።

 

የቤቶች ልማት ኤጀንሲ በየአካባቢው በአቋቋማቸው ጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ አበዳሪ ባንኮች ገንዘብ መሰብሰቡን ለመሥራት በወረዳ ደረጃ ሥርዓቱ ቢዘረጋም ኅብረተሰቡ የመክፈል አቅም ስላጣ መንግሥት በከፍተኛ ችግር ላይ ወድቋል ብለዋል።

 

ምንጮቹ እንደገለጹት ዕጣ የወጣላቸው ሰዎች አንዳንዶቹ ምንም ዓይነት ገቢ የሌላቸው በመሆናቸው መክፈል የማይችሉ ሌሎቹ የመጀመሪያ ክፍያ እንኳ መክፈል ባለመቻላቸው ቤቱን ያልተረከቡ ሲሆን፣ በየክልሉ ያሉ ቤቶች ባዷቸውን ቆመው ገዢ አጥተዋል።

 

ባንኮች በኮንዶሚኒየም ቤቶችና ግለሰቦች ሕንፃዎችን ለመሥራት ከፍተኛ ገንዘብ ተበድረው መክፈል ባለመቻላቸው በርካታ ሕንፃዎችን የወረሱ ሲሆን፣ ሕንፃዎችም ገዢ በማጣታቸው ባዷቸውን ቆመዋል። ችግሩ የመንግሥት ባንኮችን ለኪሣራ የዳረገ ሆኗል ብለዋል።

 

በ1997 በየዓመቱ ለ30 ሺህ አባዋራዎች በአዲስ አበባ ብቻ የኮንዶሚኒየም ቤቶች እደላ ይደረጋል ቢባልም ባለፉት 4 ዓመታት ከ30 ሺህ ላልበለጡ አባዎራዎች ነው እድላ የተደረገው።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ