Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 24 ቀን 2001 ዓ.ም. July 31, 2009)፦ የጤና ጥበቃ መ/ቤት፤ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም፣ መንግሥትና ህዝብ ከእነሱ የሚጠብቀውን ተግባር አልፈጸሙም በማለት በርካታ የጤና ባለሙያዎች ሕግ ፊት ለማቅረብ እንደሚፈልጋቸው አስታወቀ።

 

ይኸው በመገናኛ ብዙኀን የተሰራጨው ማስታወቂያ የሙያ ግዴታቸውን ሳይወጡ “ተሰውረዋል፣ ጠፍተዋል፣ የደረሱበት አልታወቀም …” ያላቸውን የበርካታ ሜዲካል ዶክተሮችን ስም ዘርዝሯል። እነዚሁ የተሰወሩና ተፈላጊ የሆኑ ዶክተሮች በአብዛኛው ከኦሮሚያና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ከአማራ ክልል ኦሮሚያ ዞን ሆስፒታሎች፣ የጤና ጣቢያዎችና ኬላዎች በተለያየ ጊዜ ሥራቸውን እየጣሉና ለሚመለከትው አካል ሳያሳውቁ የጠፉ ናቸው ተብሏል።

 

ኢትዮጵያ ከግንቦት ወር 1983 ዓ.ም. እና በተለይም ከ1997 ዓ.ም. ምርጫ በኋላ ባለው ጊዜ፤ የደሞዝ ማነስን፣ የምቾት አለመጠበቅንና የሥልጣን አሰጣጥ በዘርና በትውልድ መሆንን በመቃወም አያሌ ባለሙያዎቿ ከመንግሥት ተቋማት ወደ ግሉ ሴክተር ከመግባታቸውም ተጨማሪ፤ በ10 ሺዎች የሚቀጠሩትም ምድራቸውን እየለቀቁ በባዕድ ሀገር እንደሚገኙ ይታወቃል።

 

አሁን የአቶ መለስ አገዛዝ “ተሰወሩ” ያላቸውን የጤና ባለሙያዎች “እየፈለግኳቸው ነው …” ይበል እንጂ ጥቂት የማይባሉት ወደ አፍሪካዊቷ ሀገር ቦትስዋና፣ ወደ ዲሞክራቲክ ጋና የተቀሩትም ወደ አውሮፖና አሜሪካ ብሎም መካከለኛው ምሥራቅ የተሰደዱ መሆኑ ይፋ ሆኗል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ