የቅንጅት ሥራ አስፈጻሚ የፓርቲውን አዲስ ስም ሰየመ
(ሰበር ዜና)
Ethiopia Zare (እሁድ የካቲት 30 ቀን 2000 ዓ.ም. March 9,2008)፦ በብርቱካን ሚደቅሣ የሚመራው የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከላእላይ ም/ቤት በተሰጣቸው ኃላፊነት መሰረት ዛሬ ለቅንጅት አዲስ ስያሜ መስጠታቸውን ታማኝ ምንጮቻችን ከአዲስ አበባ ገለጹ።
የቅንጅት ሥራ አስፈጻሚ ቅንጅትን በአዲስ ስም ለማስመዝገብ የመስራች አባላት የፊርማ ማሰባሰቢያ ቅጽ እንዲሰጣቸው ለምርጫ ቦርድ ማመልከታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ምርጫ ቦርዱም ቅጹን ለመስጠት የድርጅቱን ስያሜ አቅርቡ ባላቸው መሰረት ዛሬ የሥራ አስፈጻሚው በአዲሱ ቢሮ በመሰባሰብ የድርጅቱን ስያሜ "አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ" እንዲሆን መወሰኑን ለማወቅ ችለናል።



