ኃይሌ ገብረሥላሴ ራሱን ጡረታ አወጣ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

እሁድ ጥቅምት 28 ቀን 2003 ዓ.ም. (ኖቨምበር 7 ቀን 2010 እ.ኤ.አ.) በኒው ዮርክ ማራቶን ከ27ኛው ኪሎ ሜትር በኋላ በቀኝ እግሩ ጉልበት ላይ በደረሰበት ከፍተኛ ሕመም ምክንያት ውድድሩን አቋርጦ የወጣው አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ራሱን ከአትሌቲክስ በጡረታ ማግለሉን በዚህ በጋዜጣዊ መግለጫው አስረድቷል። ለወጣቶቹ ቦታ መልቀቅ አለብኝ ሲል ተደምጧል። (ጋዜጣዊ መግለጫውን ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

ታላቁ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሐንስ - ገሞራው

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ታላቁ ገጣሚና ባለቅኔ ኃይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው) አሁንም በስደት በስዊድን መዲና ስቶክሆልም ይገኛል። አንዳንዶች ይህ ታላቅ የኢትዮጵያ ሀብት በሕይወት መኖሩን አያውቁም፣ የት እንደሚኖር የማያውቁም አሉ። ይህ ቪዲዮ በስዊድን የኢትዮጵያ ሙዚቃና ድራማ ቡድን ለታላቁ ገጣሚና ባለቅኔ ያበረከተለት ነው። በዚህ ቪዲዮ ላይ ያለው ሙዚቃ ደራሲ ዘነበ በቀለ ሲሆን፣ ምስልና ድምፅ ቅንብሩ ደግሞ በስዊድን የኢትዮጵያ ሙዚቃና ድራማ ቡድን ነው። ቪዲዮው የተዘጋጀው ሐምሌ 2002 ዓ.ም. (ጁላይ 2010 እ.ኤ.አ.) ነው።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!