አቶ አሚን ጁንዲ የኦነግ አመራር በሲያትል ያደረጉት ንግግር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አቶ አሚን ጁንዲ በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦሮሞ ነጻነት ግንባር ዋና ጸሀፊ ሲሆኑ በሲያትል ከተማ ግንቦት ሰባት አባል የሆነበት ጥምረት እና ኦነግ በጋራ በጠሩት ህዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ አነጣጠረና ተሰብሳቢውን ህዝብ ያስደመመ ንግግር አድርገዋል። (ንግግራቸውን በቪድዮ ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!)

ፕ/ር ሙሴ ተገኝ ስለሻዕቢያና ስለአርበኞች ግንባር ተናገሩ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ፕ/ር ሙሴ ተገኝ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባርን ከመሰረቱት 6 ሰዎች ውስጥ አንዱ ሲሆኑ፣ በዚህ በያዝነው ሣምንት እጅግ አስገራሚ ቪዲዮ አሰራጭተዋል። ፕ/ር ሙሴ ሻዕቢያ የኢትዮጵያ አፍራሽ እንደሆነ እና የአርበኞች ግንባር ከኤርትራ ምድር መውጣቱን በዚህ ቪደዮ ገልጸዋል። የፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ መንግሥት የአርበኞች ግንባር ታጋዮችን እየቀጠቀጠ ”ድንጋይ ጠባቂ፣ ሽንኩርት አምራችና ከታፊ፣ የሰው ላብ ዘራፊ በማድረጉ፣ እንዲሁም ድርጅቱን በመከፋፈልና የተለያዩ ስሞች በመስጠት፣ የግንባሩ አመራሮች ያልፈቀዱትን ውህደት ፈጽመዋል በማለት፣ ...” ግንባሩ የሚያካሂደውን ትግል እያደናቀፈው በመሆኑ ከኤርትራ ጠቅልሎ ወጥቷል በማለት ፕሮፌሠሩ ገልፀዋል። የፕ/ሩን መግለጫ ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!

የጨካኙና የአረመኔው ጆሴፍ ኮኒ አደን

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ጆሴፍ ኮኒ በኡጋንዳ ከ60 ሺህ በላይ ሕፃናትን ጠልፏል

Ethiopia Zare(ዓርብ የካቲት 30 ቀን 2004 ዓ.ም. March 9, 2012)፦ የኡጋንዳው የጎሬላ ተዋጊዎችና "የጌታ ተጋዳይ ሠራዊት" (Lord’s Resistance Army - LRA) መሪ የሆነውን ጨካኙንና አረመኔውን ጆሴፍ ኮኒን ለማደን በኢንተርኔት የተሰራጨው የ30 ደቂቃ ቪዲዮ በአራት ቀን ውስጥ በዩቲዩብ ብቻ ወደ 60 ሚሊዮን ተመልካቾችን ማግኘቱ ታወቀ። የቪዲዮው ዓላማ ጨካኙን በዓለም ላይ ታዋቂ በማድረግ በቁጥጥር ስር ለማዋል ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብጹዕ አቡነ መቆርዮስ ለወጣት የኔሰው ገብሬ ዓለም አቀፍ የፀሎት ጥሪ አስተላለፉ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ብጹዕ አቡነ መቆርዮስ በካናዳ ባደረጉት ቃለምልልስ ለመምህር የኔሰው ገብሬ ዓለም አቀፍ የፀሎት ጥሪ አስተላልፈዋል። ሙሉውን ቃለምልልስ በሁለት የቪዲዮ ክፍሎች የቀረበ ሲሆን፤ ሁለቱን ክፍሎች ከዚህ በታች ያገኙዋቸዋል። ለማየትና ለማዳመጥ የማጫወቻ ቁልፎቹን ይጫኑ!

ክፍል አንድ

ክፍል ሁለት

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!