ምርጫው አቶ ምርጫው
ምርጫው አቶ ምርጫው
ከ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ያምር ይሆን እንዳማረላቸው
መርጠው ሲመረጡ ዓምና ያየናቸው
አገሩን ባልጠቅስ ስሙም ባይነሳ
የነሱን አይተናል እንዴት ነው የኛሳ
ነፃነት አሟልቶ ፍቃድን ያደለ
ወይንስ እኔ ነኝ ወሳኙ ግዴታን ያዘለ
እኩል ፉክክር ነው በሁሉም ተመራጭ
ወይስ ላንዱ ክብር ሰጪ ሌላውን ለገሳጭ
የተወነው መንገድ ምርጫውን ለመራጭ
ወይስ መንገድህ ይሄ ነው የሌለበት ልዋጭ
ተፎካካሪውን የሚያከባብር ነው
97ቱን ደግመን ልናየው ነው
ፖለቲከኞቹ ከዚያ ተምረዋል
የከርሞውን ምንጣፍ ዘንድሮ አንጥፈዋል
ኦባማ ክሊንቶን በፉክክር ከርመው
አብረው እንደሠሩ እኛም ልንሠራ ነው
ከምርጫው በኋላ አሸነፍኩኝ ያለ
ሊያስር ሊገርፍ ነው ወይንስ ሌላ አለ
ምርጫና መመረጥ ባገሩ ባይከፋም
ውጤቱን በፀጋ መቀበል ሰውን አያሳማም
አዋቂም አልጠፋ ከኢትዮጵያም አይጠፋ
ደኅና መሪ መምረጥ ዕድሉ ከሰፋ
ተመራጭ ላገሩ ቢያስብ ቅኑውን
ቢቆሮቆር ለህዝብ አይቶ የሌላውን
አንጎልን ከማሰር ማየት ከጠቀመ
ላገር የሚበጅን ለመሥራት ካለመ
አፈፉን ገፈፉን ሆድ ከሚሸከመው
ጥርት ያለውን ጠጅ ብንጠጣ ምነው
ከብዙ ይጠራል ከጠራም ያፈራል
የቀና እንደሆነ ምርጫም ዋጋ ያወጣል
ወንድምን ከኋላ እንዳያድግ ከመሥራት
ከፊት ለፊት ማድረግ የነቃ ውይይት
ለጊዜው ነው እንጂ ወንድሙን ያስከፋ
ታሪክ ይገለዋል ቢወለድም ይፋ
የተፈጥሮን መንገድ ማን ሰው ችሎ አገደ
ምርጫና መመረጥ ሞተም ተወለደ
የተሰበሰበን እንበላ እንደሁ እንጃ
ተካፍሎ መብላቱ አይሁንብን ፍርጃ
ፈራጅ ይፈረድበታል ቅን ወይም ጠማማ
የጁን ሰው አያጣም የሆነው በሁሉም ቢሰማ
ወይ ራስ እምሩ ወይ ራስ መሥፍን
ምረጥና ግባ ሁሉም ያው የጁን
አልመርጥም አትበል ምረጥ ወይ ተመረጥ
ያበሻ ልጅ ደንቡ ወይ ምረጥ ወይ ቁረጥ
ወዲህ ወዲያ አትበል እንዳልሞላ እንሥራ
ቀጥ ብለህ ተወጣ በጀመርከው ጎራ
ጎራው ብዙ ይችላል እንደየዘሩበት
ስንዴ ዘርቶ ገብስ አይጠየቅ ከመሬት
ስንዴ የዘራ ሰው ጎራው ይዟል ስንዴ
ያበቀለው ስንዴ የሚያጭደውም ስንዴ
የሚበላው ስንዴ የሚያበላው ስንዴ
እንኳን ላገሩ ሰው ለሚለውም ጓዴ
ላዩን ስንዴ መሰሎ እንክርዳድ ከሆነ
የቀመሱት ጊዜ ያው ራሱን ተካነ
አካፋ የዶማን እንደምን ይሠራል
ከእንጨትም ቀጥ ያለው ለዘንግ ይመረጣል
ምርጫው ምርጥ ልጁ ካረገህ ፈጣሪ
ያቢሲኒያን ዘንግ የሚስጥህ መሪ
ፍርድህ እኩል ይሁን አመራርህ ቀና
ያገርህን ቀዬ ጠብቅ አስማማና
አልነግርህ ድንበሩን አንተው ታውቀዋለህ
ምላሰ ጉዑዟ መሬት አለች ያበሻ ያለህ
እርሻው ይጠበቃል በጎበዞች ማማ
ያ ጎበዝ እረኛ ከነቃ ከሰማ
ለይቸ አልነግርህም ማማው ያለው በጅህ
ተመረጥ በምርጫው እንዲነቃ ልጅህ
ላገር የሚበጀን ምርጫው እንዲመርጠው
ጎበዙን እረኛ መማማህን አስይዘው
ምርጫው ካላችሁኝ ሰሜን ካነሳችሁ
እንደ ስሜ ሥሩ አቶ አሰኝታችሁ
ከ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.



