“ገበጣ ገበጥባጣ”

ቦጋለ ዳኜ - ከካሊፎርንያ

“ገበጣ ገበጥባጣ

ከኢየሩሳሌም የመጣ”

 

 

ብቻውንም ቢሆን

ሁለት እጅ ካለው

ማጨብጨብ ይችላል

ብቻውን አንድ ሰው።

 

ነገር ግን ስንመጣ

ወደኛው ገበጣ

ቢኖርም ሁለት እጅ

ከሌለ አጣማጅ

ጨዋታ መች ሊኖር?

ጠጠር መቆጣጠር።

 

ጅም ካለ በጠጠር

ባጉል አጀማመር

ዞሮ ዞሮ አይቀር

ባዶ ቤት ማለት ቊር!

 

ጅም ካለ በጠጠር

ስሉስ ባይሸሽ ነገር

ነክህን ወዘተ ...

ጭቅጭቅም ቢኖር

አዕምሮ ነው ዳኛው

ጨዋታው እንዳይቀር።

 

አለበለዚያማ

ከተጀመረማ

ጠጠር መሰራረቅ

ይቀራል ጨዋታው

ባጉል መጨቃጨቅ።


ቦጋለ ዳኜ - ከካሊፎርንያ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ