ያንተ እንጀራ

ወለላዬ ከስዊድን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

(ግጥሙን በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

በሀገርና በመልካችን፣

በዘር ሀረግ ውልደታችን፣

አንድነትም ብንጋራ፣

ይቀፈኛል የአንተ እንጀራ።

 

አንተ ሀገርን ህዝብን ክደህ፣

ከግፈኞች ጋር አብረህ፣

በሀብትና በሥልጣን ጥም፣

ተጨማልቋል እጅህ በደም።

ሺህ ገዳይ ነህ መቶ አሳሪ፣

ህሊና ቢስ ሆድ አዳሪ።

እኔ ያንተን የሆድ ስፋት፣

የህሊና ታዛዥነት፣

አልጋራም ደህና ሰንብት።

ያንተ ዘር ነኝ አትበለኝ፣

አይደለሁም ዞር በልልኝ!

ብሰደድም ኖሬም ብራብ፣

አንተን ሆኜ እኔን ሳስብ፣

ስለዳንኩኝ ከመሽቆጥቆጥ፣

ደስተኛ ነኝ ካንተ ይበልጥ።

በሀገርና በመልካችን፣

በዘር ሐረግ ውልደታችን፣

አንድነትም ብንጋራ፣

እኔ አልቀምስም ካንተ እንጀራ።

የግፍ ሥራ መጨረሻ፣

እንዴት እንደሁ ማጣቀሻ፣

ምሳሌ አድርጎ ከፈጠረው፣

ያንተ አይነቱ አንዱ እኮ ነው።

እኔ አላምንም በኩነኔ፣

ግፈኛውን እዚህ በዓይኔ፣

አይቻለሁ ምድር ወድቆ፣

በራሱ ደም ተጨማልቆ።

በሀገርና በመልካችን፣

በዘር ሐረግ ውልደታችን፣

አንድነትም ብንጋራ፣

ይቀፈኛል የአንተ እንጀራ።


ወለላዬ ከስዊድን

 

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ