እንቅልፍ! (ገ/ኢ. ጐርፉ)
ገ/ኢ. ጐርፉ
በውድቅት ሌሊቱ
ከሞቀው አልጋዬ
በወቅቱ፣ በሰዓቱ
ብርድ-ልብስ ደርቤ
ተከናንቤ
ሃሳቤ እሹሩሩ ...
ብቻውን ነጐደ!
ያላበው ገላዬ
በቅዠት አበደ
እንቅልፍ እንጅሩ!
ስወራጭ፣ ሳልተኛ፣
ስገላበጥ ክፉኛ
አጉል ነጋብኛ ...
እንቅልፍ የት አባቱ
ሄደ …
ቢሮ ገብቼ ግን ሥራ ሲያፋጥጠኝ
ወይ ስቃዬ!
ሳልሞት፣ በውኔ
ቁጭ ብዬ ወንበር ላይ
ፍዝዝ ይላል ዓይኔ
አለቃዬ
ዓይን-ዓይኔን ሲያይ
ወይኔ፣ ወይኔ!
ነቅቶ መቀመጡ
እምቢዮ ይለኛል
ዓይኔን መግለጡ …
ያቅተኛል
ሽልብ ያደርገኛል …
ምን አባቱ!
ገ/ኢ. ጐርፉ



