ገ/ኢ. ጐርፉ

ነዪ በሰፈሬ ዘወይ በይብኝ እባክሽን

ውዴ አትጨክኝብኝ ቢደረደር

መርፌ አይሆንም ማረሻ ቀዳዳው

ጠፋብኝ ከፍቅርሽ መሸሻ።

 

ስምሽን ስጠራው ሆዴ ይዋልላል

‘ዋ! ታመልጥህና ይቆጭሃል!’ ይላል

ቢደረደር መርፌ አይሆንም ማረሻ

እቱ ላንቺ ፍቅር አጣሁኝ ማርከሻ።

 

ግራ፣ ቀኙ ገደል የለውም መንገድ

ካንቺ ተለይቼ ወየት ነው የምሄድ?

ቢደረደር መርፌ አይሆንም ማረሻ

ካንቺ ተለይቼ አጣሁኝ መድረሻ።

 

እስቲ ዓይኗን ልየው ደፍሬ፣ ቀርቤ

ሳላያት ከዋልኩኝ ይጨነቃል ልቤ

ቢደረደር መርፌ አይሆንም ማረሻ

ፎቶሽን ላኪልኝ ልቤን ማስታገሻ።

 

አብሬያት አድሬ ሕልሜ ነው በውኔ

መለየት አቃተኝ፣ ወይኔ! ወይኔ!

ቢደረደር መርፌ አይሆንም ማረሻ

ጠረንሽ ወረረኝ ሆኖኝ ማስታወሻ።

 

ገ/ኢ. ጐርፉ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ