ለምን? Why? ኤፍሬም እሸቴ

ለምን ይኼ ሆነ - ለምን ያ አልኾነም፣
ለምን እንዲህ ሆንን - ለምን እንዲያ አልሆንም፣
ጥያቄ ጥያቄ ዛሬም እንደ ትናንት፣
መልሱ ላያረካ - ጠብ ላይል ካንጀት፣
ለምን ይሉት ቋንቋ - ለምን ይሉት ነገር፣
ፍጻሜ የሌለው - የጥያቄ ክምር፣
"ለምንድነው አንበል ..." ቢልም ባለቅኔው፣
የሚሰማው ሳይኖር ይጠየቃል ይኼው።

(ኤፍሬም እሸቴ፤ ፉብሩዋሪ 25/2013፤ ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ሀገረ ማርያም - ሜሪላንድ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ