የአማራው መከራ ላገሩ ስለሠራ
ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ
እንሁን ቀና ሰው፣ እውነት እንናገር፣
ለእውነት ጥብቅና፣ ሃቁን አስቀድመን፣
ፖለቲካን ወዲያ፣ ትንሽ አቆይተን፣
እስቲ እንተባበር ሃሰት ላይ አድመን።
እኮ የታለ ፍርድ፣ የታል'ኮ ፍትህ፣
የታለ ባገሩ የሕግ አስከባሪ፣
ኧረ የታል መንግሥት፣
መቅሰፍት የሚሆነው ላገር አሸባሪ?
እንዲህ የሚበድል፣ ማን ነው ውጣ የሚል
ማን ባቀናው ምድር፣ ማንን ከማን ሃገር?
እንዴት የ'ትዮጵያን ልጅ ከ'ትዮጵያ ተነቀል?
ለሰሚ ግራ ነው፣ የሚያሰቅቅ ነገር።
"አማራ" በሚል ሥም
የጠሩት ገበሬ፣
ምን ጥፋት አጠፋ፣
ባዶ አፈር በገፋ በጥማዱ በሬ?
ላቡን እያዘራ ትንፋሹ እስኪያጥር
"ሆ! በሬ" እያለ ካመት ዓመት አርሶ፣
ልጆቹን ባበላ ራሱ ኩርማን ጎርሶ?
ነግዶ በኖረ ላገር ሳይሆን ሸክም፣
ግብር በገበረ ሊጠቅም መንግሥትን፣
በዜግነት ግዳጅ ዋትቶ፣ ወ'ቶ ቢያድር፣
ለምን ይዳረጋል እንዲያጣ እርስትን?
ከ'ባብና ከጊንጥ፣ ከጋሬጣ ታግሎ፣
አሜኬላ ወግቶት፣ ጫካውን መንጥሮ፣
ያለማውን መሬት ለምን ይነጠቃል?
ያፈራውን ቅሪት ግሮ ተጣጥሮ? (... ሙሉውን ግጥም በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! ...)



