ዮሴፍ ዘካናዳ

የጨርቋን ጫፍ ጥለት
በአቧራ ነትቦ ባንዲራ ያለበት
ጭምድድ አርጎ ይዞ ህፃኑ ጠየቀ
ግራ ቀኝ እያየ እየተሳቀቀ
"አገራችሁ ሂዱ" ሰዎቹ የሚሉን
የት ነው አገራችን?
ጥለትሽ ላይ ያለው ያገርሽ መለያ
የት ናት ኢትዮጵያ?
የት ጋር ተጀምራ የት ጋር ነው ምታልቀው?
አፈርና ወንዙ ባህል ኃይማኖቱ የት ጋር ነው ሚለየው?

 

 

እዚህ አይደለችም? ወደምንሄድበት እዚያናት ኢትዮጵያ?
ወጥተን ነበር እንዴ ከናታቻን ጉያ?
ውስጥ ሆነን ውጭ ነበርን?
እንደዚ ጨክነው አጣድፈው ሚገፉን
ወዴት ነው ምንሄደው?
ወዴት ናት አገሬ?
ወጥተን ነበር እንዴ ከአገር ከድንበሬ?
ኧረ ቆይ እማማ
እስቲ ልጠይቅሽ ጉዳችንን ልስማ
ታላቅ ወንድማችን እውጪ አገር ሚኖረው
እሱም ይባረራል? ጦቢያን ይፈልጋል?
ንገሪኝ እማማ?
ይሄን ነገር ልስማ?!


ዮሴፍ ዘካናዳ 06/04/2013
ወደ" አገራችሁ" ሂዱ ለተባሉት ህፃናት መታሰቢያ ትሁን

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ