ሰርካለም ፋሲል Serkalem Fasil

"አንተ የኔ ጀግና ነህ። ብትሞትም ሙት፣ በእውነትህ ኮርተህ ሙት!" አለች ሰርካለም እንባ እየተናነቃት ..."

ፍርደ ገምድል ዳኛ!
ለምለም ፀጋው
ለፍርደ ገምድል ዳኛ

ደራሲው በል ድረስ

ዘፋኙም በል ዝፈን

ሙሾህን ዘልሰህ አቀንቅን አደራ፤

 

እንደ ጥጃ ምስል አርጎ በሙት የሚገዛ

ከኢትዮጵያ በቀር ማን አለ ፈዛዛ

የሙትን ፎቶግራፍ

እንደ ልሻን ለብሶ ኮርቶም የሚያቅራራ።

ፍርደ ገምድል ዳኛ

ፍርደ ገምድል ዳኛ ሸንጎ ላይ ታየ አሉ አጉል ተንቆራጦ፣

ለስክንድር ጽሁፍን ለአንዱዓለም ፍትህን

ለማስተማር ቆርጦ፤

ፍርደ ገምድል ዳኛ የአርባ ጦም ጸሎትን በተግባር ገለጸ

የኢትዮጵያን ልጆች

ጾሙ ሳይገድፍ በግዞት አቆረ ለሥጋ ቋምጦ።

ፍርደ ገምድል ዳኛ

እህቴ ሰርካለም እንባሽን ጥረጊ በርች በኃይማኖት፣

አሳርጊም ጸሎት፤

ማርያምስ ይቅርታ አርጋየል

ልጇን ሲሰቅሉባት።

 


© ለምለም ፀጋው፣ May 3, 2013

በአቶ ወሰን ሰገድ ገብረ ኪዳን ጽሁፍ "የእነ አንዱአለም እና እስክንድር ነጋ ነገር በጠቅላይ ፍ/ቤት" የተነሳሳ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ