ክንፈሚካኤል ገረሱ
ጋራ ሸንተረርሽ አረንጓዴ ለብሶ፣
ያ ፍልቅልቅ ገጽሽ ዳግም ተመልሶ፣
ሰላም ብልጽግና እንደ አደይ አብቦ።
ረሃብ ድንቁርና ታሪክ ተረት ሆኖ።

ይታየኛል እማ!


ስትሞናደይ ቀን በቀን ስትፈኪ ኮርተሽ በልጆችሽ፣
ዓለም ሲያቀዳጅሽ የመቻቻል አክሊል፣
ዳግም ስትሆኝ ኃያል የሥልጣኔ አስኳል።
የብዙሃን ፀሐይ የእኩልነት ጮራ፣
ቅጥርሽን ሲያደምቀው ከዳር ዳር ሲያበራ፣
የሰላም የፍትህ የአንድነት አዝመራ፣
ሲያሸት ሲጎመራ።

ይታየኛል እማ!


ክንፈሚካኤል ገረሱ

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ